December 2, 2024 – VOA Amharic
የአዉሮፓ ኅብረት አዲሷ ከፍተኛ ዲፕሎማት ካጃ ካላስ እና ባልደረባቸው የአዉሮፓ ምክር ቤት ኃላፊ አንቶኒዮ ኮስታ ወደ ሥልጣን በመጡ የመጀመሪያ ቀን ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ዛሬ እሁድ እለት ኪቭ ገብተዋል።
አንቶኒዮ ኮስታ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት “ከዩክሬን ጋር እንደምንቆም ግልፅ መልዕክት ለመስጠት ነው የመጣነው ሙሉ ድጋፋችንን እንቀጥላለን” በማለት ተናግረዋል።