የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ በዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ በዋስትና እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መወሰኑ ተገለጸ፡፡
ዛሬ በዋለው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቶ ታዬ በዋስትና እንዲፈቱ መወሰኑን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
በዚህም መሰረት የቅርብ ቤተሰባቸው እንዲለቀቁ የሚያስፈልጉ ሂደቶችኝ በማስፈጸም ላይ እንደሆኑም ነው የተነገረው።