የኦሮምያ ክልል መንግስት የሰላም ስምምነት የተፈራረመው በቡድኑ ቅቡልነት ከሌለው አመራር ጋር ነው” ሲል በጃልመሮ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትአስታወቀ።

መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ባወጣው መግለጫ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው ጃልሰኚ ነጋሳ እንደማይወክለው ገልጿል፡፡
የተደረገው ስምምነት ከቡድኑ ጋር የተደረገ ስምምነት አድርጎ እንደማይወስደውም ነው ቡድኑ የጠቆመው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ትላንት ህዳር 22 ቀን የሰላም ስምምነት የፈረሙት ከወራት በፊት በስነምግባር ጉድለት ካባረርኳቸው አመራር ጋር ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አስታውቋል።
የኦሮምያ ክልል መንግስት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥ ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል የሰላም ስምምነት ፈርመዋል ሲል መግለጹ ይታወቃል።
ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አፈንገጠው የወጡ ተደርጎ በመንግስት በኩል እየቀረበ ያለው መረጃ ፍጹም ሀሰት ነው ሲል የገለጸው መግለጫው የህዝቡን ስነልቦና ለመግዛት በሚል በመንግስት በኩል የቀረበ ማታለያ ነው ሲል ተችቷል።