
ከ 7 ሰአት በፊት
ከኒው ዮርክ ወደ ፓሪስ ሳትከፍል ተደብቃ የተጓዘችው ግለሰብ ማንነቷ ታወቀ።
ግለሰቧ የ57 ዓመቷ ስቬታላና ዳሊ ትባላለች።
አሁን የምትገኘው ፈረንሳይ ሲሆን፣ ወደ አሜሪካ ላለመመለስ ውዝግብ መፍጠሯ ተዘግቧል።
ትኬት ሳትቆርጥ በዴልታ አየር መንገድ በኩል ከኒው ዮርክ ጄኤፍኬ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ፓሪስ ቻርልስ ደ ጉል አውሮፕላን ማረፊያ የተጓዘችው ግለሰብ ሩስያዊት መሆኗ ተገልጿል።
ቪዛ ስለሌላት ፈረንሳይ ለመግባት እንዳልተፈቀደላት የፈረንሳይ ፖሊስ አስታውቋል።
እስካሁን ክስ አልተመሠረተባትም።
በጄኤፍኬ አውሮፕላን ማረፊያ የኤሌክትሮኒክ ፍተሻ መሣሪያን አልፋለች። መታወቂያና የበረራ ትኬት አይተው የሚያሳልፉ ተቆጣጣሪዎችንም ማለፍ ችላለች።
የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ የደኅንነት ሠራተኞችን ጠቅሶ እንዳለው የበረራ ትኬት የሌላት ግለሰብ የተከለከሉ እቃዎች ሳትይዝ ማለፏ ታውቋል።
እንዴት ጥበቃዎችን አልፋ አውሮፕላኑ ውስጥ እንደገባች ግን አልታወቀም።
- የሙሴቬኒ ቀንደኛ ተቃዋሚ እንዴት ከኬንያ ተሰውሮ በኡጋንዳ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተገኘ?ከ 8 ሰአት በፊት
- አራት ጊዜ ከእስራኤል የአየር ጥቃት ብታመልጥም ልጆቿን ያጣችው እናትከ 8 ሰአት በፊት
- ለአስርታት ሲፈላለጉ የቆዩት አባት እና ልጅ ሳያውቁ በፌስቡክ ላይ ጓደኛሞች ሆነው ተገናኙከ 8 ሰአት በፊት
ዴልታ ባወጣው መግለጫ “ከደኅንነት በላይ ዋጋ የሚሰጠው ነገር የለም። ዴልታ ጥልቅ ምርመራ እያደረገ ያለውም በዚህ ምክንያት ነው። እስከ መጨረሻው ድረስ ከሌሎች የአቪዬሽን ባለድርሻ አካላትና የሕግ አካላት ጋር በትብብር እንሠራለን” ብሏል።
ጋርዲያን እንደዘገበው፣ ግለሰቧ አውሮፕላኑን ከተሳፈረች በኋላ ከሽንት ቤት ወደ ሽንት ቤት እየተዘዋወረች ቆይታለች። ወንበር ላይ አለመቀመጧን የበረራ አስተናጋጆች ዘግይተው ደርሰውበታል።
አብራሪው የፀጥታ ባለሙያዎች ግለሰቧን ከአውሮፕላን ለማስወረድ እንደሚሄዱ ሲናገር ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምሥል ያሳያል።
“ካፕቴናችሁ ነኝ። ፖሊሶች እየመጡ ነው። አውሮፕላኑ ውስጥ መኖር የሌለበትን ሰው መጥተው እስከሚወስዱ ድረስ የተቀሩት ተጓዦች እንዲጠብቁ ነግረውናል” ሲል ይደመጣል።
ከተጓዦቹ አንዱ ለሲኤንኤን በሰጠው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ግለሰቧ ወደ ኒው ዮርክ የሚመመለስ አውሮፕላን አቅራቢያ ሁከት ስታስነሳ ይታያል።
“አሜሪካ መመለስ አልፈልግም። ዳኛ ብቻ ነው አሜሪካ ሊመልሰኝ የሚችለው” ስትል ይሰማል።
ምን ማለት እንደፈለገች ግልጽ አይደለም። ቢቢሲም የተንቀሳቃሽ ምሥሉን ትክክለኛነት በገለልተኛ ወገን አላጣራም።