December 3, 2024 – VOA Amharic
ትግራይ ክልል ውስጥ ዐድዋ ከተማ፣ አንዲት አዳጊን አግተው በመውሰድ መግደላቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ “ጥፋተኛ” የተባሉ ሁለት ተከሳሾች፣ አንደኛው በሞት አንደኛው ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ፣ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የዋለው ችሎት ፈረደ።
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ዐድዋ ከተማ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ የቋንቋ ትምሕርት ወደ ምትከታተልበ…