‹‹መለስ ዜናዊ በእናቱ ጎጃሜ ነው…››
‹‹ብልጽግና የትግራይን ስልጣን መረከብ አለበት››
የቀድሞ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ዩሀንስ ገብረመስቀል

ጀነራሉ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የመፍትሔ ሀሳብ አቀረቡ፡፡ በትግራይ የተባባሰው ውጥረት እንዲረግብ የፌዴራሉ መንግስት የትግራይን ስልጣን ይረከብ ሲሉ ጀነራሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ይህን ያሉት ጀነራል ዩሐንስ ገብረ መስቀል ናቸው፡፡ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ የነበሩት ሌተናል ጀነራል ዩሀንስ የፌዴራሉ መንግስት የትግራይን ስልጣን እንዲረከብ የጠየቁት ውረቶች መባባሳቸውን ተከትሎ ነው፡፡
በትግራይ ነገሮች እየተባባሱ ነው፡፡ በዛሬው እለትም ጌታቸው ለመቀሌ ሁለተኛ ከንቲባ መሾማቸውን ተከትሎ ደግሞ ፍጥጫው ይበልጥ ተካሯል፡፡ ባለፈው ሳምንት አቶ ጌታቸው ረዳ የፌዴራል መንግስት ክልሉን ሊረከብ እንደሚችል ፍንጭ መስጠታቸውን ይታወቃል፡፡ በዛሬው እለት ደግሞ የቀድሞ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ የነበሩት ጀነራል ዩሐንስ ገብረመስቀል ብልጽግና የትግራይን ስልጣን እንዲረከብ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ በተደጋጋሚ ለስቃይ የተዳረገው በሚጠሉት ሰዎች በመመራቱ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን በመውቀስ ጭምር የተናገሩት ጀነራሉ፤ ‹‹መለስ በእናቱ ጎጃሜ ባባቱ ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው›› በማለት ተናግረዋል፡፡
የሕወሓት ታጋይ የነበሩት እና በኋላም በመከላከያ ሰራዊት የመረጃ መምሪያ ዋና ኃለፊ የነበሩት ሌተናል ጀነራል ዩሐንስ፤ በቅርቡ ባሳተሙት አዙሪት በተሰኘ መጽሀፋቸው የትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ያደረጉትን ጥረት ዘርዝረዋል፡፡ ከውጪ የመጡ አካላት እና ኢሳት ሚዲያ ችግሩን አባብሰውታል ሲሉ የከሰሱም ሲሆን፤ ባሁኑ ወቅት በትግራይ ያለውን አስከፊ ቀውስ ለመፍት የፌዴራል መንግስቱ ጣልቃ ገብነት የግድ አስፈላጊ ነው በማለትም አብራርተዋል፡፡ ‹‹የትግራይ ህዝብ ዘላለሙን ከውስጡ ሲጠቃ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ አሁንም እየተጠቃ ነው፡፡ በጣም አስፈሪው እና አስደንጋጩ ነገር ደግሞ የትግራይ ህዝብ ችግር በተጋሩ ሊፈታ እንደማይችል ገሀድ የወጣ ሀቅ ነው፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ መንግስት በቃ ብሎ ሀላፊነት ሊወስድ ይገባል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን የመንግስት አለኝታነው ወዴት አለ ተብሎ መጠየቁ የማይቀር ነው›› በማለት አብራርተዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ የተበደለው በሚጠሉት ሰዎች መመራቱ ነው ሲሉ አዙሪት በተሰኘ አዲስ መጽሐፋቸው የጠቀሱት ጀነራል ዩሐንስ፤ ለዚህም አቶ መለስ ዜናዊን ዋና ተወቃሽ አድርገዋል፡፡ ምንጩ አንዳፍታ ሚዲያ ነው።