December 5, 2024 – Konjit Sitotaw 

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ሰዎችን ጭኖ ይጓዝ በነበረ አንድ አይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተናገሩ በመጥቀስ ዶቸቨለ ዘግቧል።

ተሽከርካሪው ሰኞ’ለት ጥቃቱ የተፈጸመበት አጋምሳ ከተባለ ከተማ ወደሌላ አካባቢ በመጓዝ ላይ ሳለ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት ደሞ፣ በጥቃቱ አምስት ሰዎች ተገድለው ኹለቱ እንደቆሰሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በሰዎቹ ላይ ጥቃቱን ያደረሱትን ታጣቂዎች ማንነት ዘገባው አልጠቀሰም።