December 8, 2024 

ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ውክልናቸውን አንስቼባቸዋለኹ ባላችው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትት ጌታቸው ረዳ ምትክ፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጄኔራል ታደሠ ወረደ እንዲተኩ ሰሞኑን ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር በተደረገ ስብሰባ ጠይቆ እንደነበር መስማቱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ዐቢይ ግን የደብረጺዮን ቡድን ያቀረበውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉት ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ዐቢይ በዚኹ ስብሰባ ላይ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራውን እንዳይሠራ የደብረጺዮን ቡድን እንቅፋት ኾኗል በማለት ወቅሰዋል ተብሏል። የደብረጽዮን ቡድን ግን፣ ጌታቸው ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትነታቸው መነሳት አለባቸው በሚለው አቋሙ አኹንም እንደጸና መኾኑን ምንጮቹ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

በጌታቸው ምትክ ማን መሾም እንዳለበት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እየተነጋገረ መኾኑን የደብረጺዮን ቡድን ለወራት በተደጋጋሚ ሲናገር እንደነበር አይዘነጋም።