December 25, 2024 – Konjit Sitotaw 

ባለፉት 9 ቀናት ከአማራ ክልል የመጡ ከ18 በላይ ግለሰቦች ታስረው ከከረሙ በኃላ ምስክሮች ናችሁ ተብለው በጠቅላይ አቃቤ ህግ በልደታ ፍርድ ቤት በአማራ መብት ታጋዮች፣ ምሁራንና ጋዜጠኞች ላይ እንዲመሰክሩ ቢቀርቡም በማን ላይ እንደምንመሰክር አናውቅም ተከሳሾችን አናውቃቸውም በማለታቸው ከሳሽ አቃቤ ህግ እና የተደናገጠው ግፈኛው አገዛዝ በደህንነት መስሪያ ቤቱ በኩል በተጠና መልኩ እንዲመሰክሩ ምንም የማያውቁ ዜግችን በመደለያም ጭምር ከከሚሴ ከተማ አስመጥቶ በሀሰት እንዲመሰክሩ በአዲስ አበባ በማስልጠን ላይ ናቸው።

የሀሰት መስካሪዎች የስልጠና ሂደት ትኩረት ያደረገው በዶ/ር ሲሳይ አውግቸው : በጋዜጠኛ ሲሳይ ጎበዜ እና ሌሎች ተከሳሾች ላይ ጭምር ነው ብለዋል ምንጮቻችን። እነዚህ የአማራ ተከሳሾች ለእስራት የበቁት አማሮች በማንነታቸው አይጨፍጨፉ፣ አይፈናቀሉ፣ ቤት ንብረታቸው አይዘረፍ ፣ እንደሰው የመኖር መብታቸው ይጠበቅ ማለታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ነው።

ስለሆነም መላው የፍትህ ተቆርቋሪ ወገን ይህንን በንፁሃን ላይ ሊፈፀም የታቀደውን የሀሰት ምስክር ሂደት ፍርድ ቤት ከነገ ዕሮብ ታህሳስ 16-18/2017 ከጠዋቱ 3:00 ስዓት ጀምሮ በልደታ ፍርድ ቤት በመገኘት እንዲታዘቡ እና እንዲያጋልጡ እንጠይቃለን።

ፍትህ በሀሰት ለተከሰሱ የአማራ እስረኞች!!!