December 27, 2024 – VOA Amharic
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ በኤርትራ የነበራቸውን የሁለት ቀናት ጉብኝት አጠናቀዋል።
ሶማሊያ የተረጋጋች መሆኗን ማረጋገጥ የቀጠናውን ሠላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የሁለቱ ሃገራት ፕሬዝደንቶች በውይይታቸው ማጠቃለያ ላይ መግለጻቸው ታውቋል።
በቀናው ግጭትና ሁከት ከሚፍጥሩ የውጪ ጣልቃ ገብነቶች ራሱን ማላቀቅ እንዳለበት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ማሳሰባቸው…