
ከ 4 ሰአት በፊት
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቲክ ቶክ እገዳን “ፖለቲካዊ መፍትሄ” ለመስጠት እየሰሩበት በመሆኑ እንዲያዘገየው ጠየቁ።
ጠበቆቻቸው አርብ እለት ለፍርድ ቤቱ ትራምፕ “ቲክቶክ መታገዱን ይቃወማሉ” እንዲሁም “ስልጣን ከተረከቡ በኋላ ችግሮችን ለመፍታት ፖለቲካዊ መፍትሔ መጠቀም ይፈልጋሉ” ሲሉ ለፍርድ ቤት የሕግ አስተያየታቸውን አስገብተዋል።
ጥር 2 /2010 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ የቲክ ቶክ ባለቤት የሆነው ቻይናዊ ባይትዳንስ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያውን ለአንድ አሜሪካዊ ድርጅት እንዲሸጥ ወይም በጥር 11/ 2017 ዓ.ም. እገዳ እንዲጣልበት በሚለው ላይ ክርክሮችን ይሰማል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እና ሕግ አውጪዎች ቲክቶክ እና ባይትዳንስ ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው ሲሉ ቢከሷቸውም ድርጅቶቹ ግን ውንጀላውን ይክዳሉ።
በአሜሪካ ውስጥ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ ላይ የቀረበው ውንጀላ ኮንግረስ በሚያዝያ ወር ሕግ እንዲያረቅ ያደረገው ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ም ረቂቅ ሕጉን ፈርመው አጽድቀውታል።
ቲክቶክ እና ባይተዳንስ ሕጉን ተቃውመው የተለያዩ ክሶችን የመሰረቱ ሲሆን፣ ምንም እንኳ ባይሳካላቸውም የአሜሪካን የመናገር ነፃነትን ስጋት ላይ ይጥላል ሲሉ ተከራክረዋል።
እስካሁን ድረስ ኩባንያዎቹን አገዛለሁ ያለ አካል ባለመቅረቡ መተግበሪያው የመታገድ እጣ ፈንታው በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እጅ ላይ ወድቋል።
- የሱዳኗ መዲና ካርቱም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የመጀመሪያውን እርዳታ አገኘችከ 5 ሰአት በፊት
- በአሜሪካ በካቴና የታሰረ እስረኛ ከመሞቱ በፊት ፖሊሶች ክፉኛ ሲደበድቡት የሚያሳይ ቪዲዮ ወጣከ 5 ሰአት በፊት
- ሩሲያ ለተከሰከሰው የአዘርባጃን አውሮፕላን ተጠያቂ ልትሆን ትችላለች- አሜሪካከ 5 ሰአት በፊት
ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕጉ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ እግድ እንዲያደርግ የቀረበለት ጥያቄ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረ ሲሆን፣ ቲክቶክ፣ ባይተዳንስ እና የአሜሪካ መንግሥት በጉዳዩ ላይ እገዳው ተግባራዊ ሊሆን ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ጥር 2/ 2017 ዓ.ም. ችሎት ፊት ቀርበው ይከራከራሉ።
ትራምፕ በጠበቆቻቸው አማካኝነት አርብ እለት ፍርድ ቤት ባቀረቡት ሕግ አስተያየት ላይ “በአንድ በኩል ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የንግግር መብትን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ ፖሊሲ እና በብሄራዊ ደህንነት መካከል ያለን ውጥረት” ይወክላል ብለዋል ።
መዝገቡ ትራምፕ “በዚህ ክርክር ላይ ምንም አይነት አቋም አይወስዱም” ቢልም የጥር 11 ቀነ ገደብ መገፋት ወደ ፍርድ ቤት ሳይሄዱ በጉዳዩ ላይ “ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲሰጡ እድል” እንደሚኖረው አክሏል።
የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ከቻይና ጋር ግንኙነት ያለው ቲክ ቶክ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ነው ሲል የተከራከረ ሲሆን፣ በርካታ መንግሥታት ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ላይ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።
በሞንታና ኦስቲን ክኑድሰን የሚመራው እና በርካታ አቃቤ ሕጎችን ያካተተው ቡድን ባይትዳንስ እና ቲክ ቶክ ድርሻቸው ለሌላ እንዲሸጡ ወይም እንዲታገዱ የሚያስገድደው ሕግን እንዲያጸድቀው ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳስበዋል።
በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ የፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሕጉን ለመሻር የተደረገውን ሙከራ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
ትራምፕ በመጀመሪያ የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ቲክቶክ መታገድ አለበት ብለው የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን እገዳውን እንደሚቃወሙ በይፋ ተናግረዋል።
በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ “ለቲክቶክ በልቤ ውስጥ ጥሩ ቦታ አለኝ ፣ ምክንያቱም የወጣቶችን ድምጽ በ 34 ነጥቦች አሸንፌያለሁ” ብለዋል።
አክለውም “ቲክቶክ ከዚህ ጋር የሚያገናኘው ነገር አለ የሚሉ አሉ” ብለዋል።