December 29, 2024 – Konjit Sitotaw
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የክልሉን ፖሊስ አዛዦችና የዞንና የወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችን አሳፍረው ይጓዙ በነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ላይ ሰሞኑን ፈጸምኩት ባለው ጥቃት በርካቶችን መግደሉን አስታውቋል።
ቡድኑ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ፈጸምኳቸው ባላቸው ጥቃቶች በርካታ ወታደሮችን መግደሉንና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር እንዲስተጓጎል ማድረጉንም ገልጧል።
ቡድኑ፣ በጉጂ ዞንም አንድን ወህኒ ቤት በመቆጣጠር፣ 20 የፖለቲካ እስረኞችን አስለቅቄያለኹ ብሏል።
ቡድኑ በተጠቀሱት አካባቢዎች ፈጸምኳቸው ያላቸውን ጥቃቶች ከነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልተቻለም።