
ከ 2 ሰአት በፊት
ሰኞ ታኅሳስ 21/ 2017 ዓ.ም. በተለይም በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ 10 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል።
በአገሪቱ ከ2017 አዲስ ዓመት ጀምሮ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተደገጋገሙ እና ንዝረታቸውም እስከ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ድረስ እየተሰማ ይገኛል።
የዘርፉ ባለሞያዎች በተለይም ወርሃ መስከረም እና ጥቅምት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የነበሩባቸው ወራቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።
በኅዳር ወር ጋብ ብሎ የነበረው ርዕደ መሬት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ሲሆን፤ ከእስካሁኑ በሬክተር ስኬል ከፍተኛው ርዕደ መሬት የታየውም ባለፉት ቀናት ነው።
የኢትዮጵያ የርዕደ መሬት መመዝገቢያ መረብ ኃላፊ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ተፈጥሯዊው ክስተት “ፀጥ” ብሎ ቆይቷል፤ ነገር ግን እንቅስቃሴው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሬክተር ስኬል እስከ 5.1 ደርሷል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከእሁድ ታኅሳስ 20/2017 ዓ.ም. ከሰዓት ጀምሮ “ጎላ ጎላ ያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ ባሕሪዎች እያየን እንገኛለን” ብለዋል።
ተፈጥሯዊ ክስተቶችን የሚያጠናው እና የሚመዘግበው የአሜሪካ የጂኦሎጂ ሰርቬይ በኢትዮጵያ ትናንት ሰኞ ታኅሳስ 21፤ በ24 ሰዓታት ብቻ 10 ርዕደ መሬቶች መከሰታቸውን መዝግቧል።
ሰኞ ጠዋት 03፡51 አዋሽ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.6 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፤ ሌሊት 10፡38 ላይ ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ አዋሽ አካባቢ ርዕደ መሬት ተከስቷል።
ርዕደ መሬቱ መተሀራ አካባቢ ሦስት ጊዜ፤ አቦምሳ የተባለ አካባቢ ደግሞ ሁለት ጊዜ እንዲሁ ተከስቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጦች በኢትዮጵያ መደጋገማቸው እና አቅማቸው መጠናከሩ ፍርሃትን እና ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፤ ረ/ፕ አታላይ ግን “መደናገጥ አያስፈገልግም” ብለዋል።
“[ንዝረቱ] እስከ አዲስ አበባ ድረስ ሊሰማ ይችላል። ግን በጉዳት ደረጃ [አዲስ አበባ] እስካሁን የተመዘገበ የለም። ወደፊትም በ150፤ 160 ኪ.ሜ በላይ ሄዶ ጉዳት ያደርሳል ብለን አንጠብቅም። ብዙ መደናገጥ አያስፈልግም። [ርእደ መሬቱ የተከሰተባቸው አካባቢዎች] መጠነኛ ጉዳቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህን ደግሞ በመስክ በትክክል ሄዶ ማጥናት ያስፈልጋል” ሲሉ ሙያዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።
- “ባርነት እንደሆነ ነው የሚሰማህ” – በምያንማር ውስብስብ የወንጀል መረብ የተጠለፉት ኢትዮጵያውያን30 ታህሳስ 2024
- ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊጉ ሊወርድ ይችላል – ሩበን አሞሪምከ 6 ሰአት በፊት
- ቻይና የኮቪድ መረጃን ይፋ እንድታደርግ የዓለም ጤና ድርጅት አሳሰበከ 6 ሰአት በፊት
አፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ትምሕርት ቤቶችን ጨምሮ መንገዶች እና ቤቶች በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአካባቢው ባለስልጣናት በምስል አስደግፈው ተናግረዋል።
ቢቢቢ ያላረጋገጣቸው ከሰሞኑ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች የተለቀቁ ምስሎች አንዳንድ መኖሪያ ቤቶች ላይ ርዕደ መሬቱ ያስከተላቸው ጉዳቶችን አሳይተዋል።
ይዘቱን Facebook ይፈቅዳሉ?
ይህ ጽሑፍ በFacebook. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የFacebook ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።Accept and continue
ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።
የ Facebook ይዘት መጨረሻ
“በአካል ተገኝቶ ባህሪው ምን ይመስላል? የጉዳት መጠኑስ እንዴት ነው? የሚለው በደንብ መጠናት ይኖርበታል። ግን ለክፉ ይሰጣል ብለን አንጠብቅም” ሲሉ ፕ/ር አታላይ የጉዳት መጠኑ መጠናት እንዳለበት ጠቁመዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በሬክተር ስኬል እስከ 9.5 የሚደርስ ርዕደ መሬት “ከፍተኛ” የተባለ ደረጃን የሚይዝ ነው ሚሉት ባለሞያው፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት 6̇.8 ሬክተር ስኬል የሆነ ርዕደ መሬት መከሰቱን ተናግረዋል።
ፕ/ር አታላይ ሰሞነኛ ክስተቶች “መካከለኛ” ደረጃ የሚሰጣቸው ርዕደ መሬቶች መሆናቸውን ጠቁመው፤ ርዕደ መሬቶቹ የሚከሰቱባቸው ስፍራዎች ግን የጉዳት ደረጃቸውን እንደሚወስኑት ገልፀዋል።
“ጉዳት ለማድረስ መሀል ከተማ ከተፈጠረ 3.0 ሬክተር ስኬል [ጉዳት] ሊያደርስ ይችላል። የተፈጠረበት ቦታ የት ነው? የሚለው እንጂ አሁን የተፈጠረው ከፍተኛ ነው የሚባል አይደለም” ሲሉ አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ የርዕደ መሬት ክስተት ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ሲናገሩም፤ “ከዚህ ከፍ ሊል የሚችልበትም እድል ይኖራል፤ እየቀነሰ ሊሄድም ይችላል። በቅርብ ጊዜ [ግን] የሚያቋርጥ አይመስልም” ብለዋል።
“. . .ያጠራቀመውን ኃይል አሁን በያዘው መልክ አስተንፍሶ ይቆማል። በተለያየ ጊዜ እንደዚህ አይነት ክስተቶች የተለመዱ ናቸው። ምንም አዲስ ነገር አይደለም” ሲሉ መተማመኛ ሰጥተዋል።