December 31, 2024 – VOA Amharic
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ትላንት እሑድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የጂሚ ካርተርን ሕይወትና ሥራ ለረዥም ዓመታት በቅርበት ሲከታተል የቆየው የአሜሪካ ድምጹ ኬን ፋርቦ፣ የቀድሞውን ፕሬዝደንት የፖለቲካ ሕይወት እንዲሁም ሥልጣን ከለቀቁ በኋላ፣ በጤና እና ዲሞክራሲ መስክ ለዓለም ያደረጉትን አስተዋጽኦ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ቃኝቷል።