December 31, 2024 – VOA Amharic
በአፋር ክልል፣ ዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ ርእደ መሬት መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊሲክስ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታወቀ።
የተቋሙ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ፣ ርእደ መሬቱ ያስከተለው ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።