የጃዋር መሃመድን መጽሃፍ አላነበብኩም አልገዛም ግዛው ለገሰ
የሚል ስም በመጽሃፉ ዙሪያ ከተነሳ የእኔ አለመሆኑ ይታወቅልኝ።
ስለ ጃዋር የማነበው ብዙም አለተስማማኝም፤ ጃዋር አልጸጸትም ሲል ከዚህ በፊት በጽሁፍም በንግግርም የተናገራቸውን ነገሮች እንደገና መርምሮ የሚጸጸትውነገር እንዳልሰራ መናገሩ ነው። ጃዋር ግን ብዙ ኢትዮጵያውያንን የሚያስቀይሙ ነገሮች ተናግሯል – በሜንጫ እንቀላቸዋለን፤ ኢትዮጵያ አውቶ ኦፍ ኦሮሚያ፤ ተከበብኩ፤ ኮዬ ጨፌ ጥቂቶቹ ናቸው።
ሰሞኑን እንደገለጥኩት ጃዋር እና እኔ በኢትዮጵያ ላይ ያለን አገራዊ እይታ በጣም ይለያያል; ትዝ ካላችሁ ከሁለት ከሶስት አመት በፊት 20 ምናምን ያለው ጽሁፍ በኦሮምኛ ጽፎ ትርጓሜውን አንቤዋለሁ።
ሶስት ትላልቅ ነጥቦቹ
- ብልጽግና ዴሞክራቲክ ባይሆንም ስልጣን ከእጃችን እንዳይወጣ መጠንቀቅ አለብን፤
- በኢኮኖሚው የኦሮሞ ድርሻ ማደግ አለበት እና ከተሞች ይዘታቸውን መለወጥ አለባቸው የሚሉት ትዝ ይለኛል።
- ከዛም ለስልጣን የሚያሰጋን አማራው ስለሆነ የትግራይ ፖለቲከኞችን ለመጠቀም መስራት እንዳለባቸው ጽፏል።
ዛሬም ጃዋር አብይ የሚተቸው ለስልጣን እንጂ አገር ለማዳን ነው ብዬ አላምንም ያ ቢሆን ኖሮ ይጸጸት ነበር።
ያም ሆኖ የጃዋር መመለስን ለፖለቲካ መጠቀም ጥሩ ፖለቲካ ይመስለኛል፤ በብልጽግና ላይ የሚሰነዛራቸው ትችቶች ጃዋርን የሚሰሙ ሰዎችን ከብልጽግና ካሸሻቸው ጥቁም አብይን ለሚፋለሙ ሃይሎች ነው፡፤ ግልጽ ለመሆን የጃዋር ሎሌዎች ደጋፊዎች አጨብጫቢዎ እንሁን ማለቴ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፍጻሜ በሃይል ሚዛን የሚወሰን መሆኑን ተቀብሎ መደራጀት. መታጠቅ፤ አንድ መሆን ቅድሚያ ተሰጥቶት ዋነኛውን ጠላት የሚያዳክሙ ሃይሎች ሲመጡ ቢያንስ ዝም ማለት ይሻላል ባይ ነኝ! Gizaw Legesse