January 1, 2025 

ምርጫ ቦርድ፣ ሕወሓት እስከ የካቲት 3 ቀን ድረስ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ አሳስቧል።

ቦርዱ፣ ፓርቲው በሕጉ መሠረት ጉባዔውን ከማድረጉ ከ21ቀናት በፊት ጉባዔውን የሚያካሂድበትን ትክክለኛ ቀን እንዲያሳውቅም ታኅሳስ 17 ቀን በጻፈው ደብዳቤ ማሳሰቡን ገልጧል።

ፓርቲው በሕግ የተቀመጠውን ግዴታ በወቅቱ ካልፈጸመ ግን፣ ተገቢውን ውሳኔ እንደሚሰጥ ቦርዱ አስጠንቅቋል።

ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ግድም አካሄድኩት ላለው ጠቅላላ ጉባዔ፣ ቦርዱ ዕውቅና ሳይሰጠው እንደቀረ አይዘነጋም።