January 1, 2025 – Konjit Sitotaw
48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል
ነገሩ እየከፋ ነው። ለምሳሌ ዛሬ ብቻ ከ21 በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ “Zamyad” የተባለ መተግበሪያ ላይ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።
በዚህ መተግበሪያ መሰረት ዛሬ ምሽት ከደቂቃዎች በፊት የተከሰተውን ጨምሮ ሁለት እጅግ አደገኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።
ትላንት 18 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን የዛሬውን ከትላንቱ ጋር ስንደመር በአጠቃላይ 48 ሠዓት ሳይሞላው 39 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ መተግበሪያው ላይ ያለው መረጃ ያሳያል። ከታች ይመልከቱት ።
