January 1, 2025 

የትግራይ ክልል የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፣ በሥራ አጥነት ሳቢያ ከክልሉ በአማካይ በወር 32 ሺሕ ወጣቶች በሕገጥ መንገድ እንየተሰደዱ መኾኑን እንደገለጠ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በሕገወጥ መንገድ ከተሰደዱት ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ቤተሰቦች፣ ልጆቻቸው ባኹኑ ወቅት በሊቢያ በሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ተይዘው በአሰቃቂ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ኹለት ቤተሰቦች፣ ሊቢያ ላይ ለተያዙ ልጆቻቸው ማስለቀቂያ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር እንደተጠየቁና ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በልጆቻቸው ላይ አሰቃቂ ድብደባ ሲፈጽሙ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደተላኩላቸው ተናግረዋል ተብሏል።

ቢሮው፣ በክልሉ የወጣቶች ሕገወጥ ስደት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን መናገሩንም ዘገባው አመልክቷል።