January 1, 2025 – Konjit Sitotaw 

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ በምትገኘው ቦዶዴ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው አማጺ ቡድን ትናንት ምሽት 12 ሰዓት ገደማ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ ሰባት የመንግሥት ታጣቂዎች እንደተገደሉና በርካቶች እንደቆሰሉ  ከአካባቢው ነዋሪዎች ተሰምቷል።

የቡድኑ ታጣቂዎች በከተማዋ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ለሰዓታት ካደረጉ የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ፣ የሠራዊቱ አባላት አካባቢውን መቆጣጠራቸውን ምንጮች ገልፀዋል።

በምዕራብ ጉጂ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቡድኑ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ እየፈጸመ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች፣ በዚሁ ምክንያት ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደተስተጓጎሉ ገልጸዋል።

ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው፣ የክልሉ መንግሥት የቡድኑ አንድ ክንፍ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እየገቡ እንደኾነ እየተገለጸ ባለበት ወቅት ነው።