ሳምንት ባስቆጠረው የሸዋ ተጋድሎ የተመታው የአገዛዙ ሠራዊት አስከሬኑን በሁለት ተሳቢ ጭኖ መውጣቱ ተገለፀ።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ራሳ ግንባር ባለፉት ሳምንታት በተደረገ ከፍተኛ የአውደ ውጊያ ውሎ ክፉኛ የተመታው የአገዛዙ ጨፍጫፊ ሠራዊት በሁለት ተሳቢ ሙትና ቁስለኛ አስከሬኑን ይዞ ወደ ሸዋሮቢት ከተማ ገብቷል።
ከታሕሳስ 17 ጀምሮ ከተለያየ አቅጣጫ ያለውን ኃይል አሰባስቦ ቀወት ወረዳ ራሳ ለመግባት በማፉድና ሳላይሽ ተራራ ላይ መሽጎ ወደ ራሳ ለመግባት ሙከራ ያደረገውን ኃይል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ራምቦ ክፍለጦር እና አባት አርበኛ ሠራዊት ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ምሽጉን እስኪለቅ ድረስ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል።
ምሽጉን የለቀቀው የጠላት ሠራዊት መግባት እንደ መውጣት የሚል መስሎት ፤በወታደራዊ ጠበብቶች ውሳኔ የተለቀቀለትን ቦታ አገኘሁ ብሎ ዘው ብሎ ከገባ በኋላ ለ9 ቀናት በከበባ ሲቀጠቀጥ ውሀና ተተኳሽ የሚያቀርበልት ደጀን አጥቶ ከራሳ አርበኞች፣ከራምቦ ክፍለጦር፣ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፋለጦርና በፋኖ ለማ አስማማው የሚመራ የእዙ ተወርዋሪ ሻለቃ የተረፈው በረሀብና በውሃ ጥም አልቋል።
ይህንን የማያውቀው ቤት ገብቶ መውጫ የጠፋበትን የአገዛዙ ልቅምቃሚ ሠራዊት ለማትረፍ ከኬሚሴ እና ከደብረብረሃን ከተማ ተጨማሪ ሀይል ቢያሰማራም ከደብረብረሃን የተነሳው የጠላት ሠራዊት ጣርማበርና ቀይት ላይ በአስቻለው ደሴ ክፍለ ጦርና በአፄ ዘረያዕቆብ ክፋለጦ(ጣይቱ ብርጌድ) በደፈጣና በመደበኛ ውጊያ ሲቀጠቀጥ አምሽቷል።
በሌላ በኩል ከኬሚሴ የተነሳውን የጠላት ሀይል የአስቴጎማ ክፍለጦር በወሰደው የደፈጣ እርምጃ በርካታ የጠላት ሀይል እርምጃ የተወሰደበተ ሲሆን ከደፈጣ የተረፈው አንድ የአገዛዙ ብርጌድ ሸዋሮቢት ከሚገኘው የጠላት ካምፕ ጋር ተሰባጥሮ ሳምንቱን በከበባ ሲቀጠቀጥ የነበረውን ሙትና ቁስለኛ ሰራዊት በዛሬው እለት በሁለት ተሳቢ ለቃቅሞ አውጥቷል።
በጠላት ከፍተኛ ድል የተወሰደበት፤ ከሳምንት በላይ የዘለቀው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የራሳው ግንባር ተጋድሎ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን በጠላት ሀይል ላይ ከፍተኛ የድል የበላይነት እየተወሰደ በርካታና የጠላት ኃይል በምርኮና እጅ በመስጠት ላይ ሲሆን ስርዓቱን ከድተው የሚቀላቀሉ የአገዛዙ ሠራዊት አባላትም ይገኙበታል።
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ