
ከ 1 ሰአት በፊት
በአሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በበረዶ ውሽንፍር መመታቸውን ተከትሎ ሰባት ግዛቶቿ የአስቸኳይ ጊዜ አወጁ።
በአገሪቱ በአስር ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የክረምት አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ቅዝቃዜ እና በረዶ ያስከትላል የሚል ትንበያን ተከትሎ ከ60 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አሜሪካ እንዲጠነቀቁ መመሪያ ተላልፏል።
አብዛኛው የካናዳ እና ከካንሰስ እስከ ኢስት ኮስት ያሉ 30 የአሜሪካ ግዛቶች በዚሁ የአየር ሁኔታ ማንቂያ ስር እንደሆኑ የብሔራዊ የአየር ትንበያ አገልግሎት (ኤንደብልዩኤስ) አስታውቋል።
ከኦሃዮ እስከ ዋሽንግተን ባሉ ግዛቶች ከ15-30 ሴንቲሜትር ክብደት ያለው በረዶ እንደሚጥል ይጠበቃል።
ይህንንም ተከትሎ ኬንታኪ፣ ቨርጂኒያ፣ ዌስት ቨርጂኒያ፣ ካንሰስ፣ አርካንሰስ እና ሚዞሪ ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል።
በተለምዶ ሞቃት የሆነችው ፍሎሪዳ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እንደሚያጋጥማት ይጠበቃል።
ይህ የከፋ የአየር ጠባይ የተከሰተው በሰሜንና የደቡብ ዋልታዎች የመጣ እና በአርክቲክ አካባቢ በሚዘዋወረው ቅዝቃዜ እንደሆነ ትንበያ ሰጪዎች ይናገራሉ።
- “ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም” የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርከ 1 ሰአት በፊት
- ፖለቲከኛው ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩከ 4 ሰአት በፊት
- በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ምን አይነት ጥንቃቄ ልናድርግ ይገባል?ከ 6 ሰአት በፊት
የቅዝቃዜ ማዕበሉ የአሜሪካ ምስራቅ የባህር ዳርቻን ይመታል ተብሎ ይጠበቃል። የሰሜናዊ ኒውዮርክ ግዛቶች እስካሁን 3 ጫማ እርዝማኔ ያለው የበረዶ ግግር አጋጥሟቸዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ በበኩሏ ከ5-9 ኢንች እርዝማኔ ባለው የበረዶ ግግር ተሞልታለች። የከተማዋ ከንቲባ ቢያንስ እስከ መጪው እሁድ ምሽት ድረስ የሚቆይ የበረዶ ድንገተኛ አዋጅ አውጀዋል።
ከሶስት ወራት ገደማ በፊት በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸነፉትን ዶናልድ ትራምፕን ስልጣን ለማረጋገጥ ምክር ቤቱ በመጪው ሰኞ ከሰዓት በኋላ ሊሰብሰብ አቅዷል። ነገር ግን ይህንን የከፋ የአየር ጠባይ ተከትሎ አንዳንድ የህግ አውጭዎች ከምርጫ ክልላቸው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዳያስተጓጉለው ተፈርቷል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በርካታ የባቡር አገልግሎቶች ተሰርዘዋል።
የአሜሪካ፣ ደልታ፣ ሳውዝዌስት እና ዩናይትድ የአየር መንገዶች የበረራ መስተጓጎሎች ሊያጋጥም ይችላል በሚል የሚያስከፍሉትን ዋጋ እየከለሱ ይገኛሉ።