
ከ 7 ሰአት በፊት
የገና በዓል ሲመጣ ቤተልሔም ትኩረት ትስባለች። ቤተልሔም ኢየሱስ ክርስቶ የተወለደባት ከተማ ናት።
በየዓመቱ ከተማዋ በዓሉን ለማክበር በሚመጡ ክርስቲያኖች ትደምቃለች። እርግጥ ነው አብዛኞቹ ምዕመናን ወደ ተቀደሰችው ከተማ የሚያቀኑት ለገና በዓል ብቻ አይደለም።
በኢየሩሳሌምም ሆነ በናዝሬት እንዲሁም በገሊላ ባሕር አቅራቢያ ተገኝተው የተለያዩ ሃይማኖታዊ በዓላትን ያከብራሉ።
ለመሆኑ ክርስቲያኖች ወደ እነዚህ ቅዱስ ስፍራዎች ማቅናት የጀመሩት መቼ ነው?
የሃይማኖት መፃሕፍት እንደሚያስረዱት ክርስቶስ “ቅዱስ ስፍራ” የሚባል የለም ሲል አስተምሯል። ነገር ግን በሦስተኛው ክፍለ ዘመን እንደ አሌክሳንደር እና የኢየሩሳሌም ጳጳስ ያሉ ታዋቂ ክርስቲያኖች መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ ስፍራዎችን ማሰስ ጀመሩ።
በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የክርስትና ፀሐፊው ጀስቲን ማርቲር ኢየሱስ በተወለደባት ቤተልሔም አንድ ዋሻ እንዳለ ያውቅ ነበር።
በመፅሐፍ ቅዱስ በያዕቆብ መልዕክት ላይም ይህ ተጠቅሷል።
በርካታ ፀሐፊዎች የክርስትና ቅዱስ ስፍራዎች በተለያዩ ቦታዎች እንዳሉ አስፍረዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ በቤተልሔም ቢያንስ አንድ ቅዱስ ስፍራ እንዳለ ይጠቅሳሉ።

ዋሻ ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት
መፃሕፍት እንደሚጠቁሙት ሌሎች የክርስትና ቅዱስ ስፍራዎችም በጥንት ጊዜ የተገኙ ናቸው።
ከጥንታዊቷ የኢየሩሳሌም ከተማ ወጣ ብሎ ስለሚገኘው የደብረ ዘይት ተራራ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን እንደተፃፈ ይነገራል።
በኢየሩሳሌም ከተማ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተቀበረበት እና በሦስተኛው ቀን ከሞት ስለተነሳበት መቃብር በሁለተኛው ክፍለ ዘመን እንደተፃፈ ይታመናል።
በአራተኛው ክፍለ ዘመን የተገኙ አራት ቤተ-ክርስቲያኖች ውስጣቸው ያለው ዋሻ በእጅ ተጠርቦ የተሠራ ነው። መላዕክት የጌታን መወለድ ያበሰረቡት በቤተልሔም የሚገኘው የእረኞች ሜዳ፣ ደብረ ዘይት ተራራ ላይ የሚገኘው ቤተ-ክርስቲያን፣ ክርስቶስ በይሁዳ የተካደበት ጌቴ ሴማኒ እንዲሁም የገሊላ ባሕር ይጠቀሳሉ።
በናዝሬት ከተማ ደግሞ መላዕክት ለማርያም ታላቁን መልዕክት ያበሰሩበት ስፍራ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ያደገበት ቤት ይገኛሉ።
ሁሉም የአራተኛ ክፍለ ዘመን አብያተ ክርስቲያናት ከዋሻ ጋር ተያይዘው የተገነቡ አሊያም ዋሻ ውስጥ ያሉ ናቸው።
- በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኦሮቶዶክስ ክርስትያኖች የገና በዓልን እንዴት እንደሚያከብሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችከ 9 ሰአት በፊት
- የገና በዓል የሚከበርበት ዕለት ለምን ተለያየ? ታኅሣሥ 29 የሚያከብሩት አገራት እነማን ናቸው?7 ጥር 2025
- ራሳችንን ከአደገኛ የምግብ መመረዝ እንዴት መጠበቅ እንችላለን?7 ጥር 2025

በሥነ-ቅርስ ጥናት የተደገፈ
የሥነ-ቅርስ አጥኚዎች እነዚህን ቦታዎች መርምረው የሰጡት ትርጉም ዋሻዎቹ ለቤተ-ክርስቲያን ጥቅም እንዲሆኑ ሆነው መፈልፈላቸውን ነው።
ይህ ትርጓሜ በበርካታ መፅሐፍት የተደገፈ ነው።
ዩስቢየስ “የቆስጠንጢኖስ ሕይወት” በተሰኘው መፅሐፉ በአራተኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ሦስት ግዙፍ አብያተ-ክርስቲያናት የተገነቡት በመፅሐፍ ቅዱስ ትልቅ ስፍራ ባላቸው ቦታዎች ነው። እነዚህም ቅዱስ መካነ መቃብር፣ ቤተክርስቲያን፣ የክርስቶስ ልደት ቤተ ክርስቲያን እና “ኤሌዎና” ናቸው።
ዩስቢየስ በመፅሐፎቹ እኒህ አብያተ ክርስቲያናት ከዋሻ መሠራታቸውን የሚያሳዩ ዝርዝር መረጃዎች አስቀምጧል።

ሃይማኖታዊ ጉዞ
ሰባቱ የዋሻ አብያተ-ክርስቲያናት ከክርስትና ጋር ያላቸው ጥምረት ከአራተኛው ክፍለ ዘመን በፊት የመጣ ቢሆኑም እስካሁን በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው።
የአብያተ ክርስትያናቱ አገነባብ መለያየት እና ቅርፃቸው አለመመሳሰሉ የተለያዩ ሰዎች እንደገነቧቸው ይጠቁማል።
ወደእነዚህ ቤተ-ክርስቲያኖች ሃይማኖታዊ ጉዞ የተጀመረው ከአራተኛው ክፍለ ዘመን በፊት እንደሆነ የሚጠቀሙ ማስረጃዎች ይላሉ።
ሕንፃዎቹ በአራተኛው ክፍል ዘመን እንደ ቤተ-ክርስቲያን ከማገልገላቸው በፊት ምዕመናን ወደ ስፍራዎቹ ይጓዙ ነበር።
በፅሑፍ የተቀመጡ እና የሥነ-ቅርስ ምርምር ውጤቶች እንደሚያሳዩት ሃይማኖታዊ ጉዞ የተጀረመው ሰዎች ከሚያስቡት ጊዜ ቀደም ብሎ ነው።
ይህ ማለት ቤተ-ክርስቲያናቱን የገነቡት ሰዎች ቅዱስ የሚባሉ ስፍራዎችን ተከትለው የገነቡት እንጂ የፈጠሩት አይደለም። ምናልባትም አማኞች ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም ወደ እነዚህ ስፍራዎች ይሄዱ ነበር ማለት ነው።
ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያውያን ምዕመናንን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ለሃይማኖታዊ ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ያቀናሉ።
