እናት ፓርቲ፣ ርዕደ መሬት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን ባስቸኳይ ከአደጋ ሥጋት ነጻ ወደኾኑ አካባቢዎች የማስፈር ሃላፊነት የክልል መንግሥታት ሳይኾን የፌዴራል መንግሥቱ ነው ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጧል።
መንግሥት የርዕደ መሬት ክስተቱ የከፋ ጥፋት የሚያስከትልበት ደረጃ ላይ ቢደርስ፣ አደጋውን ለመቋቋም የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግም ፓርቲው አሳስቧል።
ፓርቲው፣ ለአደጋው ተጋላጭ ከኾኑ አካባቢዎች በተለይ በትላልቅ ፎቆች ላይ የሚሠሩና የሚኖሩ ሰዎች እንዳስፈላጊነቱ ለተወሰነ ጊዜ ከሕንጻዎቹ የሚወጡበት መንገድ እንዲመቻችም ጠይቋል።
ፓርቲው አያይዞም፣ መንግሥት በአገር ዓቀፍ ደረጃ የሕንጻ ግንባታ ፖሊሲ በማሻሻል ርዕደ መሬትን የሚቋቋሙ ግንባታዎች እንዲገነቡ የሚያስችል ማዕቀፍ እንዲያዘጋጅ አሳስቧል።