January 10, 2025 – VOA Amharic
የእሳት አደጋ ሠራተኞች ብርቱ ትንቅንቅ እያደረጉ ላሉበት አደገኛ የሰድድ እሳት ቃጠሎ፣ ከ130 ሺሕ በላይ የሎስ አንጀለስ አካባቢ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። እስካሁን ቢያንስ አምስት ሰዎች በአደጋው ሕይወታቸውን ማጣታቸው እና ከ1 ሺሕ በላይ ሕንፃዎች መውደማቸው ታውቋል።
ትላንት ከቀትር በኋላ ላይ አዲስ የተቀሰቀሰው እና በጥድፊያ እየተዛመተ ያለው ቃጠሎ ‘ሆሊውድ ሂልስ’ በመባ…