January 11, 2025 – VOA Amharic
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለአእዋፋት ኢንፍሉዌንዛ የተጋለጠ አንድ ሰው ህይወቱ ማለፉን፣ የሉዊዚያና ክፍለ ግዛት የጤና ባለሥልጣናት ባለፈው ሰኞ ይፋ አደረጉ።
የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በማኅበረሰብ ደረጃ ለበሽታው የመጋለጥ እጣ አሁንም አነስኛ መሆኑን ቢገልጽም፤ የአሜሪካ ድምጿ ዶራ መኩዋር ባጠናቀረችው ዘገባ እንደጠቆመችው ግን አንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች የሥጋት ድምጽ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል…
