ባንዳን የማፅዳት ስራችን ተጠናክሮ የሚቀጥል የየለት ተግባራችን ነው በተያዙ የአገዛዙ ካድሬዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወስዷል ።
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ የአዲሱ ትውልድ አቢዮት ከሰልፍ እስከ ሰይፍ በደረሰው ተጋድሎው ውስጥ ህዝባችንን በጠላትነት ፈርጀው የሀሰት ትርክት ነዝተው ሊያጠፋን ከተነሱ ጠላቶቻችን እኩል ምናልባትም አንዳንዴ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን በላይ ህዝባችንን ሁሉን አቀፍ መከራ ያደረሱበት ከህዝባችን ውስጥ የወጡ እና ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎች እንደሆኑ በትግላችንን ያረጋገጥነው እውነታ ነው ።
ብርጌዳችን በቀን 28/04/2017ዓ.ም በዳንግላ ወረዳ ጊሳ ቀበሌ ላይ ከጨፍጫፊው የብልፅግና ስርዓት ትእዛዝ ተቀብለው እና በአገው ሸንጎ መሩ የአዊ ዞን አስተዳደር በተሰጣቸው ተልኮ መሰረት ህዝባችንን ለዳግም ባርነት ለመዳረግ አለኝ የሚሉትን ሀይል አግተልትለው የገቡትን በአቶ ጌትነት ማረልኝ የቀድሞው የዳንግላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተመራ የጥፋት ቡድን ላይ በወሰደው የተቀናጀ እርምጃ ይዘውት የገቡት አራጅ ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ሲደመሰስ አቶ ጌትነት ማረልኝን ጨምሮ አራት የአገዛዙ አመራሮች ከአንድ ሹፌራቸው ጋር ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በውጊያ መሀል ጥይት ጨርሰው ተማርከው እንደነበር በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ማሳወቃችን ይታወሳል ።
ግለሰቦቹ በፋኖ ሲማረኩ የመጀመሪያቸው አይደለም ከዚህ በፊት የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ዳንግላ ከተማን በተቆጣጠረበት ወቅት በብርጌዳችን ተይዘው እና ምክር ተሰጧቸው በሀይማኖት አባቶች ፊት በፈጣሪያቸው እና በቤተሰቦቻቸው ምለው ድጋሚ ወደ ብልፅግና የጥፋት መንገድ ላይገቡ ተገዝተው በሰላም የተለቀቁ ቢሆንም በፈጣሪ ፊት የገቡትን ማህላ ክደው የብልፅግና ወንጌልን በመቀበል በተለያዩ መድረኮች ፋኖን ካለ ስሙ ስም ሲሰጡ በዳንግላ ከተማ እና በዙሪያው የአማራ ልጆች በግፍ ሲጨፈጨፉ ህፃናት የአብነት ተማሪዎች ከአንድ ቤት ሁለት እና ሶስት ሰው በግፍ ሲገደል ለዚህ ገዳይ ብድን ፖለቲካዊ ሽፋን በመስጠት አንዳንዶቹ ላይ በተግባር መሳሪያ ይዞም በመሰለፍ ህዝባችንን ሁሉን አቀፍ መከራ ሲያደርሱ የቆዩ እና ማህበራዊ እረፍት ሲነሱ የነበሩ መሆናቸው ይታወቃል ።
በተለይ በዳንግላ ወረዳ አፈሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጥቅምት 7ቀን 2017ዓ.ም የሰባት አመቱን ህፃን መዝገቡ ታደለን ጨምሮ ከ7በላይ ንፁሀን በድሮን ሲጨፈጨፉ የድርጊቱ ዋነኛ ተዋናይ በመሆን በህፃናት ሞት ሲሳለቁ የነበሩ በውጊያ ላይ አንድ አባላችን ቆስሎ ራሱን መከላከል በማይችልበት በልኩ በጠላት እጅ ሲወድቅ አይኑን አውጥተው በመኪና ዳንግላ ከተማ ማህል ጎትተው ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ ህዝብ እያየ አስክርኑ ጋር ፎቶ ሲነሱ የነበሩ ርህራሔ የሚባል ያልፈጠረባቸው ጨካኝኞች ስለሆኑ በህዝባችን ጥያቄ መሰረት እነዚህ ባንዳወች ላይ እርምጃ ቢወሰድ ለተቀሩት አስተማሪ ይሆናል ተብሎ ስለታመነበት በተያዙ የአገዛዙ ካድሬዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወስዷል ።
ለዚህም የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ሙሉ ሀላፊነቱን ይወስዳል ።ለመላው ህዝባችን እና የትግላችን ደጋፊዎች :- ጠላት በየ ሚዲያዎቹ የሚራጨው የአዞ እንባ በፍፁም ጀሮ ባለመስጠት አሁንም እንደወትሮው ትግላችሁን እና ድርጅታችሁን እንድትደግፉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
ለአገዛዙ ሆድ አደር ሚዲያዎች እና የዲጂታል ሚዲያ ሰራዊት አባላት :-ትናንት የአማራ ህዝብ በአማራነቱ ሲጨፈጨፍ እና ህዝቡ ብሶቱን በአደባባይ ሲናገር ሶፍት እናቃብላችሁ እያላችሁ ስትሳለቁብን ነበር ዛሬ የህዝባችን የውስጥ ባንዳዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ ንፁሃን ተገደሉ የሚል ጫጫታ እያሰማችሁ ትገኛላችሁ ።
በውጊያ ውስጥ የጠላት የፖለቲካ እና ወታደራዊ አመራሮች የጦርነቱ የስበት ማእከል (center fo gravity )እንደሆኑ አለም ያወቀው እውነት ነው ። ስለዚህ የፖለቲካ አመራር ሁኖ ንፁህ የለም ያውም በህዝብ ደም የጨቀዩ የዘመናችን ሔሮድሳዊያንን ስለዚህ እናንተም በተሎ ወደ እውነተኛው የህዝብ ትግል ጎን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ይህ ካልሆነ ግን ዛሬ እንዳለቀሳችሁላቸው ነገ ይለቀስላችኋል።
ከጠላት ጎን ለተሰለፋችሁ አመራሮች እና የአገዛዙ መለዮ ለባሾች ሁሉ:- በተደጋጋሚ እንዳልነው የምህረት በራችን ክፍት ነው ነገር ግን እንደቀድሞው ጓዶቻችሁ በአውደ ውጊያ ጥይት ስትጨርሱ ብትማረኩ እርምጃችን የከፋ እንደሚሆን እየገለፅን ። እስካሁን ለሆዳችሁ አድራችሁ የበደላችሁትን ህዝብ ለመካስ ፍላጎቱ ካላችሁ አሁንም የድርጅታችን የምህረት በር ክፍት መሆኑን እንገልፃለን ።
ለመላው የፋኖ አባላችን :- አላማህ የእውነት ጥያቄህም የፍትህ ፣ እኩልነት እና የነፃነት ነው ስለዚህ ፈጣሪ ከጎንህ ነው ። ግፈኞችን በእጆችህ ይጥላቸዋል አገዛዙን አሸንፈኸዋል የቀረው ቀብሩን ማፋጠን ነው እሱንም በጠላቶቻችን እለቅሶ አጅበን ግባተ መሬቱን እናፋጥነዋለን ።
እንፅና እንበርታ ከምንግዜውም በላይ አንድነታችንን እናጠናክር አሸንፈናል ።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ።
ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ
ዳንግላ