January 15, 2025 – Konjit Sitotaw 

የኑሮ ውድነቱ ዋና ዲዛይነር የብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ፣ የመለስ ዜናዊ መንግሥት የመረጠው የኢኮኖሚ ዕድገት ቅርጽ ችግር እንደነበረበት ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ከኾኑት ወይዘሮ ቢልለኔ ሥዩም ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል።

አሁን ያለው የኑሮ ውድነትና የአይ ኤም ኤፍ ፖሊሲ ጥገኝነት የፈጠረውን የራሳቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ያንቆለጳጰሱት የባንኩ ገዢ በኢኮኖሚ ዕቅዶች አመራረጥ፣ አተገባበርና በፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ችግሮች እንደነበሩበት ማሞ ገልጸዋል።

የአገሪቷን ኢኮኖሚ ያላሸቁት የአለም ባንክ ሰራተኛው ማሞ፣ ከለውጡ በፊት 70 በመቶ ገደማ የባንኮች ብድር ለመንግሥት ብቻ ይሠጥ እንደነበርና ባኹኑ ወቅት ግን 80 በመቶው ገደማ የባንክ ብድር ለግሉ ዘርፍ እየተሰጠ መኾኑን ማሞ አውስተዋል። ይህን ይበሉ እንጂ ባንኮ ምንም አይነት ብድር የማይሰጡና በርካታ ቅድመ ሁኔታ ደርድረው ደንበኞቻቸውን እያራቁ ሲሆን የባንኮች ከፍተኛ መሰናክል የሆነው ማሞ ምህረቱ የሚመሩት ብሄራዊ ባንክ መሆኑ ይታወቃል።

የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተዘው በጀት ዓመት በ8 ነጥብ 45 በመቶ ያድጋል ብሎ ተብሎ እንደሚጠብቅም በቀን ሁለትና ሶስት መመሪያ የሚያስተላልፈው የብሄራዊ ባንክ ገዢው በዶላር ተከፋዩ አቶ ማሞ ጠቅሰዋል። አቶ ማሞ ምህረቱ ሃገሪቷን የአለም ባንክ እና የአይ ኤም ኤፍ ባሪያ ካደረጉ በኋላ ደምወዝ የሚከፈላቸው ከአለም ባንክ ነው።