January 17, 2025 – ምንሊክ ሳልሳዊ 

[addtoany]

ፋሲልን ተጫወቱበት !

ፋሲልን ተጫወቱበት ! ……. ይህን ታሪካዊ ቅርስ ለማደስ አለም አቀፍ የቅርስ እድሳት ፈቃድ ሳይኖር እንዲሁም ቅርስን በተመለከተ ሙያ ያላቸው አርክቴክቶችና ሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች ባልተሳተፉበት፣ እንሳተፍ ያሉም በተከለከሉበት የተደረገ ብልጭልጭ እድሳት ነው። ፍርስራሾቹ ሳይቀር የታሪክ መሰረታቸው ተፍቆ በድጋሚ እንዲገነቡ መደረገ እጅግ አሳፋሪ ነው። …… ይህ የመንግስት ተቀጣሪ ከሆኑና እንዳይናገሩ ከተከለከሉ የቅርስ ባለሙያዎች የተገኘ መረጃ ነው። …….. የስርዐቱ አሸርጋጆችና አማሳኞች ታሪካዊ ዳራውን ሳያጠኑና በቂ የመነሻ ታሪካዊ መረጃ ሳይኖራቸው በነጩ ስለደመቀ ብቻ ሲያማስኑ ያስተዋላል። ………. ፋሲልን ከነበረበት ታሪካዊ አሻራነት በመቀየር ቅርስነቱን እንዲያጣ የተኬደበት መንገድ እጅግ አሳዛኝም አነጋጋሪም ነው። ………… በአለም አቀፍ የቅርስ እድሳት ተሞክሮዎች ውስጥ አልታየም። የቅርስ ባለሙያዎች ዝምታ እና የአማሳኞች ልፍለፋ የታሪክ አሻራን ማደፍረሱን ቀጥሏል። አስቸኳይ እርምት ካልተወሰደብት በግለሰብ ትዕዛዝ ብቻ በርካታ ቅርሶች መውደማቸውን ይቀጥላሉ። #MinilikSalsawi