January 21, 2025 – Konjit Sitotaw 

አሜሪካን አገር የስራ ፈቃድ የሌላችሁና ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ የተላለፈ መልዕክት

1) በዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ያላችሁ እና የሥራ ፈቃድ የሌላችሁ ኢትዮጵያውያን፤ ከነገ ጀምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይ ያለ ሥራ ፍቃድ የምትሰሩ ከሆናች ሁ፤ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አስራ አምስት ቀናት ከቻላችሁ መስራት አቁሙ። በዲሲ እና አካባቢው ከነገ ጀምሮ ትልቁ የኢሚግሬሽን ወረራ (raids) የሚደረግበት ነው። ወረቀት የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን የሚያሰሩ ሰዎች የዚህ (raids) ትልቁ ትኩረት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

2) በአሳይለም ላይ ያላችሁ ሁሉ እጃችሁ ላይ ዶክመንት ይዛችሁ ተንቀሳቀሱ። ለምሳሌ የሥራ ፍቃድ ያላችሁ የሥራ ፍቃድ ካርዳችሁን፣ የሥራ ፍቃድ ካርድ የሌላችሁ ደግሞ አሳይለም ፋይል ያደረጋች ሁበትን ሪሲት ይዛችሁ ተንቀሳቀሱ፤

3) ቦርደር አካባቢ የምትኖሩ ሰዎች እና ወርቀታችሁ ያልተስተካከለላችሁ ሰዎች ፥ ከቦርደር አካባቢ ራቁ። ምክንያቱም የImmigration and Custom Enforcement ኦፊሰሮች በብዛት የሚኖሩበት ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

4) ማናቸውም የኢሚግሬሽን ኬዝ ያላችሁ እና በዚህ ጉዳይ ስጋት ያላችሁ ሰዎች የኢሚግሬሽን ጠበቆችን አናግሩ። ምንም ውሳኔ ከመወሰናችሁ በፊት ከኢሚግሬሽን ጠበቆች ጋር ተማክራችሁ አድርጉ።