
ከ 7 ሰአት በፊት
የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ የሆነው ዲፕሲክ (DeepSeek) ከሰሞኑ በኢትዮጵያውያን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የቴክኖሎጂው ዘርፍ በቅርበት በሚከታተሉ ሰዎች ዘንድ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህ ቻይና ሠራሹ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ከሌሎች ተመሳሳይ መተግበሪያዎች በተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቃሚዎች አስተያየታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ሲገልጹ ተደምጧል።
ዲፕሲክ መሰል የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን በሚገዳደር ሁኔታ ዝናው በአንዴ ናኝቷል። በአውሮፓ የድርሻ ገበያ እንደ ንቪድያ፣ ማይክሮሶፍት እና ሜታ ያሉት ተቋማት መቀነሳቸው ተዘግቧል።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን በመሥራት አሜሪካን የሚወዳደራት የለም ቢባልም አዲሱ የቻይናው ተገዳዳሪ መተግበሪያ በአጭር ጊዜ አድናቆት አግኝቷል።
የተሠራው በኦፕን ሶርስ ዲፕሲክ-ቪ3 ሞዴል ሲሆን፣ አጥኚዎቹ እንዳሉት ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በታች ዋጋ ወጪ ተደርጎበት ነው የተሠራው።
ይህም ሌሎች ተፎካካሪ ተቋማት ተመሳሳይ መተግበሪያ ለመሥራት ካወጡት ገንዘብ በእጅጉ ያነሰ ነው እየተባለ ነው።
ይህ ለሁሉም ክፍት የሆነ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ ማንም ተጠቃሚ ለማወቅ የሚፈልገውን ነገር በመጠየቅ በአጭር ጊዜ በቀላሉ ዝርዝር ምላሽ የሚያገኝበት ነው።
ዲፕሲክ ቀደም ካሉት ተመሳሳይ መተግበሪያዎች የሚለየው የበርካታ ቋንቋ ሞዴሎችን በመያዝ የሚሠራ መሆኑ እየተነገረ ነው። በዚህም ምክንያት ለአገልግሎት ይፋ በተደረገ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተቀባይነት አግኝቶ የተጠቃሚዎቹ ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው።
የዚህ የቻይናውያን የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረቡ በዘርፉ የበላይነት በያዙት የአሜሪካ ተቋማት ላይ አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል።
በቻይና የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎችን የሚሠራው የቺፕ ቴክኖሎጂ ሽያጭ ላይ አሜሪካ ገደብ ለማድረግ እየሞከረች ባለችበት ሰዓት ነው ይህ መተግበሪያ የተዋወቀው።
ቺፕ ወደ ቻይና ሳይገባ ሥራውን ለማጠናቀቅ የቻይና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያዎች መረጃ በመጋራት ቴክኖሎጂውን መፍጠር ችለዋል።
ከዚህ ቀደም ያስፈልግ ከነበረው የኮምፒውቲንግ አቅም ባነሰ የሚገነቡ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያዎች እንዲገነቡም ምክንያት ሆኗል።
- ትራምፕ በወታደራዊ አውሮፕላን የተላኩ ስደተኞችን አልቀበልም ባለችው ኮሎምቢያ ላይ ታሪፍ ጣሉ27 ጥር 2025
- ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ ክብረ ወሰን በሰበረ ዋጋ ለቼልሲ ፈረመች27 ጥር 2025
- የሽንታችን ቀለም ስለጤናችን ምን ይነግረናል? ምን ዓይነት ቀለም ሲኖረው ነው ሊያስጨንቀን የሚገባው?27 ጥር 2025
ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ነተግበሪያዎችን ለመሥራት ያስወጣል ተብሎ ከሚታሰበው ባነሰ የገንዘብ ወጪ መሠራቱ የቴክኖሎጂውን የመሠራት ፍጥነት ከፍ ያደርገዋል።
ዲፕሲክ-አር1 ባለፈው ወር ከተለቀቀ በኋላ ተቋሙ ቻትጂፒቲን ከፈጠሩት ተቋማት አንዱ ከሆነው ኦፕንሶርስ ዘመነኛ ሞዴሎች “በተሻለ አቅም” ለአገለግሎት እንደሚቀርብ ተገልጿል።
እነዚህ የኦፕንሶርስ ሞዴሞች ሒሳብ፣ ኮዲንግ እና ሌሎችንም ሥሌቶችን እና ቀመሮችን ለመከወን ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው።
የዶናልድ ትራምፕ አማካሪ እና የሲልከን ቫሊ ባለ ሃብት ማርክ አንደርሰን ዲፕሲክ-አር1 “በሰው ሠራሽ አስተውሎት እንደ ስፑትኒክ ያለ አጋጣሚ ነው” በማለት አዲስ የፉክክር በር የከፈተ ክስተት ነው ብለዋል።
ስፑትኒን እአአ በ1957 ሶቭየት ኅብረት ያመጠቀችው ሳተላይት ነው። አሜሪካ በሌሎች ተፎካካሪ አገራት በሳተላይት ቴክኖሎጂ እበለጣለሁ ብላ የምትሰጋበት ነበር። አዲሱ መተግበሪያም ድንገት ገበያውን አናውጧል።
በኔዘርላንድስ ቺፕ የሚያመርተው ኤኤስኤምኤል የድርሻ ገበያው ከ10 በመቶ በላይ ዝቅ ሲል፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሀርድዌር የሚሠራው የሲመንስ ኢነርጂ የድርሻ ገበያ ደግሞ በ21 በመቶ አሽቆልቁሏል።
በሲቲ ኢንዴክስ ዋና የገበያ ተንታኝ ፊዮና ሲንኮታ “ቻይና የምታመርተው ርካሽ ምርት ገበያውን በድንገት አንገዳግዶታል። ስለዚህ የገበያ ተወዳዳሪዎችን ያስጨንቃል። በተለይም አሁን ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረጉትን የበለጠ ያሳስባል” ትላለች።
በሲንጋፖር የድርሻ ገበያ አማካሪ ቬይ-ሰርን ለቢቢሲ እንደገለጸው፣ መተግበሪያው ለአጠቃላይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንትን የሚጎዳ ነው።
የዋል ስትሪት ዋነኛ ተቋም ሲቲ በበኩሉ ዲፕሲክ እንደ ኦፕንኤአይ ያሉ የአሜሪካ ተቋማትን የሚገዳደር ቢሆንም፣ በቻይና ተቋማት የሚገጥመው ችግር እድገቱን ሊገታው ይችላል።
ባለፈው ወር የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ተቋማት ጥምረት ‘ዘ ስትራቴጂን ፕሮጀክት’ በሚል በቴክሳስ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ለመዘርጋት 500 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ አድርጓል።
- ከቢቢሲ አማርኛ ዜና እና ታሪኮች በቀጥታ እንዲላክልዎ የዋትስአፕ ቻናላችን አባል ይሁኑ5 ታህሳስ 2024
- ለኢንተርኔት ጅማሬ ምክንያት የሆነው ከ50 ዓመታት በፊት ያጋጠመው ግንኙነት መቋረጥ14 ታህሳስ 2024
- በመድኃኒት እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ ተአምር ይፈጥራል የተባለው የጉግል ፈጠራ11 ታህሳስ 2024
ዲፕሲክ በማን ተጀመረ?
ተቋሙ የተመሠረተው በአውሮፓውያኑ 2023፣ በደቡባዊ ቻይና ሀንግዡ ግዛት ውስጥ ሊንግ ዌንፌግ በተባለ ባለሙያ ነው።
የ40 ዓመቱ ባለሙያ ዲፕሲክን የሚደግፍ ተቋም ያለው ሲሆን፣ በኢንፎርሜሽን እና ኤሌክትሮኒክ ኢንጂነሪንግ ነው የተመረቀው።
አሁን ወደ ቻይና እንዳይላኩ ገደብ የተደረገባቸውን ኒቪዳ ኤ11 ቺፖች የሚያከማች ተቋም ነበረው። ወደ 50 ሺህ ገደም ቺፖችን በማጠራቀም ዲፕሲክን እንደሠራው ይታመናል።
እነዚህን ቺፖች ርካሽ ከሆኑ እና ወደ ቻይና ከሚገቡ ቺፖች ጋር በማዋሀድ ነው መተግበሪያውን የገነባው።
ዲፕሲክን የሠራው ሊንግ ዌንፌግ ከቻይና ሚኒስትሮች እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር በቅርቡ መታየቱ መንግሥታዊ እና የሌላውም ዘርፍ ድጋፍ እንዳለው ተገምቷል።
በ2024 ከቻይና አካዳሚ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ ባለሙያው እንዳለው ሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ በርካሽ ዋጋ መሠራቱ አስደናቂ መሆኑ “የተጠበቀ አይደለም።”
“የራሳችንን ፍጥነት እና ለሥራ ያወጣነውን ገንዘብ ተከትለን ነው የሚያወጣውን ዋጋ የተመነው” በማለት የዓለማችን መነጋገሪያ የሆነው አዲሱ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አመጣጥን ተናግሯል።