የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ600 በላይ ቋሚ ሠራተኞቹ ጋር የገባውን ውል በማፍረስ ሠራተኞቹን በሌሎች አራት ስኳር ፋብሪካዎች ተበተኑ ።
ሠራተኞቹ የተበተኑት፣ ፋብሪካው ያቋረጠውን ምርት በዚህ ዓመትም እንደማይጀምር ከተነገራቸው በኋላ እንደኾነ ተናግረዋል።
ሠራተኞቹ የተበተኑት፣ ወደ ወንጂ፣ መተሐራ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ኹለትና ቁጥር ሦስት ፋብሪካዎች ሲኾን፣ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የተመደቡት ግን በጸጥታ ስጋት ሳቢያ እንዳልሄዱ ተነግሯል።
በዝቅተኛ እርከን የሚገኙ ሠራተኞች ደሞ የአራት ወር ውዝፍ ደምወዝ፣ የሥራ ማፈላለጊያና ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸው ተሰናብተዋል ተብሏል።
በሌሎች ፋብሪካዎች ለተመደቡ ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው 6 ሺሕ ብር በብድር መልክ ክፍያ እንደተሠጠም ምንጮች ገልጸዋል።