
2 የካቲት 2025, 08:11 EAT
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሜክሲኮ እና በካናዳ 25 በመቶ እንዲሁም በቻይና 10 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ ዋይት ሐውስ አስታውቋል።
ትራምፕ ታሪፍ የጣሉት ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞችን ምክንያት በማድረግ ነው ብሏል።
ይህን ተከትሎ ካናዳ ሜክሲኮ በምላሹ ታሪፍ ለመጣል ዘመጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ 155 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የአሜሪካ ዕቃዎች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ መጣላቸውን እሑድ አመሻሹን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ትሩዶ ወደ አሜሪካ ከገቡ ሕገ-ወ ጥስደተኞች መካከል በካናዳ በኩል የሄዱት 1 በመቶ ብቻ ናቸው ብለዋል።
ትራምፕ ግን አገራቱ ለአሜሪካ ታሪፍ ምላሽ ከሰጡ የሚጥሉትን ታሪፍ ከፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ቻይና፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የአሜሪካ ቀዳሚዎቹ የንግድ አጋሮች ሲሆኑ ባለፈው አመት አገሪቷ ካስገባቻቸው ምርቶች 40 በመቶውን ይሸፍናሉ።
ዋይት ሐውስ እንዳለው አገራቱ “መርዛማ መድኃኒት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እንዲከላከሉ” ለማድረግ ያለመ ነው።
ትራምፕም በትሩዝ ሶሻል “በዓለም አቀፍ አስቸኳይ የምጣኔ ሃብት ውሳኔ አማካይነት ነው የተወሰነው። ምክንያቱ ሕገ ወጥ ስደተኞችን አደገኛው ፌንታኒል መድኃኒት የፈጠረው ቀውስ ነው” ብለዋል።
ታሪፍ የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት የሚያሳድግ፣ የአሜሪካውያንን የሥራ ዕድል የሚያሰፋና ከግብር የሚገኝ ገቢን የሚጨምር ነው ብለዋል ትራምፕ።
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሸንቡም ሕገ ወጥና ወንጀለኛ ስደተኞችን አስገብተዋል መባሉ “ስም ማጥፋት ነው” ብለዋል።
ዋይት ሐውስ ሜክሲኮ ከሕገ ወጥ መድኃኒት አዘዋዋሪዎች ጋር “ትስስር አላት” ሲል ከሷል።
የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት በምላሹ የኢኮኖሚ ሚኒስትራቸው ታሪፍ በመጣልና በሌም መንገድ እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ሜክሲኮ 25% ታሪፍ ትጥላለች ተብሎ ይገመታል።
- ካናዳ፣ሜክሲኮ እና ቻይና ከዛሬ ጀምሮ ታሪፍ እንደሚጣልባቸው ዋይት ሃውስ አስታወቀ1 የካቲት 2025
- የቀን ሠራተኛው ኢትዮጵያዊ በዱባይ የፋሽን ሞዴል እንዲሆን በር የከፈተለት አስደናቂ አጋጣሚ2 የካቲት 2025
- ከ20 በላይ ሴቶችን በቲንደር ያጭበረበረው ግለሰብ2 የካቲት 2025

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ “ይሄ የማንፈልገው ነገር ነው” ብለዋል።
“ለካናዳውያን ጥቅም እንቆማለን” ያሉት ትሩዶ 155 ቢሊዮን ዶላር በሚያወጣ የአሜሪካ ሸቀጥ ላይ 25% ታሪፍ እንደሚጥሉ ገልጸዋል።
የአሜሪካ ወይን፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ሽቶ፣ ልብስና ጫማ ቀረጥ ከሚጣልባቸው መካከል ናቸው።
ከታሪፍ ውጪ ሌሎች እርምጃዎችም እንደሚወሰዱ ተገልጿል።
የአሜሪካና ካናዳ ድንበር ስጋት ነው የሚለውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውድቅ አድርገዋል።
ፌንታኔል መድኃኒት በካናዳ በኩል የሚገባው ከ1% ያነሰ ነው ብለዋል።
“ታሪፍ አብረን እንድንሠራ የሚጋብዝ ጥሩ አሠራር አይደለም” ብለዋል ትሩዶ።
በዓለም ንግድ ድርጅት በኩል አሜሪካን እንደምትከስ ቻይና አስታውቃለች። ታሪፉን “በጥብቅ እቃወማለሁ” ብላለች።
የቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዲንግ ዡዌዢንግ አገራቸው ሁለቱንም አገራት የሚመጥን እርምጃ ለመውሰድ እያሰቡ እንደሆነ ገልጸዋል።
ካናዳ፣ ሜክሲኮና አሜሪካ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሸቀጥ ሽያጭ ልውውጥ ያደርጋሉ።
አንዳቸው በሌላቸው የሚጥሉት ታሪፍ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ንረት እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ናሽናል ሆምቢውልደርስ አሶሴሽን እንዳለው የቤት ዋጋ ሊጨምር ይችላል።
የአርሶ አደሮች ማኅበርም የዋጋ ንረት እንደሚከሰትና ገጠራማ አሜሪካ ያሉ ሰዎችን እንደሚጎዳ ገልጸዋል።
የአሜሪካ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ አመራሮችም በተመሳሳይ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በካናዳ እና በሜክሲኮ ላይ የሚጣለውን ታሪፍ አስመልክቶ የተናገሩት የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት “እርምጃው በአሥር ሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያንን ሕይወት የቀጠፈውን ሕገ ወጥ ፌንታኔል ምንጭ በመሆናቸው እንዲሁም በአገራችን በማከፋፈላቸው የተሰጠ ምላሽ ነው።” ብለዋል።
ሪፐብሊካኗ የቢዝነስ አማካሪ አሽሊ ዴቪስ እንደ ዋልማርትና ቦይንግ ያሉ ተቋማት ተወካይ ሲሆኑ ለቢቢሲ እንደገለጹት ትራምፕ በስደተኞች ጉዳይ መሻሻል ካዩ በሰሜን አሜሪካ ከተጣለው ታሪፍ ሊወጡ ይችላሉ።
“የድንበርና የቻይና ጉዳይ የመራጮችን ድምጽ ያገኙበት ጉዳዮች ናቸው። ስለዚህም ያሉትን ያደርጋሉ” ብለዋል።