
ከ 2 ሰአት በፊት
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና እጥለዋለሁ ያሉትን ታሪፍ ተከትሎ በዓለም አቀፉ ገበያ የእስያ ድርሻ ማሽቆልቆል አሳየ።
ባለሃብቶች የታላላቅ ኩባንያዎችን ገቢ ሊያሽመደምድ እንዲሁም አለም አቀፍ እድገትን የሚያደናቅፍ የንግድ ጦርነት ያስከትላል በሚል ስጋት ላይ ናቸው።
ካናዳ እና ሜክሲኮ አጸፋዊ የታሪፍ ምላሽ እንደሚሰጡ ሲያስጠነቀቁ ቻይና በበኩሏ “ተዛማጅ አጸፋዊ እርምጃዎችን” እንደምትወስድ እና የትራምፕን ውሳኔ በዓለም አቀፉ የንግድ ተቋም በመውሰድ እንደምትቃወመው ቃል ገብታለች።
ትራምፕ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ህገወጥ አደንዛዥ ዕጾችን እንዲሁም ፍልሰተኞችን ለማስቆም ታሪፉ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የአገራቱን ታላላቅ ኩባንያዎች የንግድ ሁኔታዎችን እንዲሁም የየዕለቱ ገበያዎችን የሚከታተሉት የሆንግ ኮንጉ ሃንግ ሴንግ 0.7 በመቶ፣ የጃፓኑ ኒኬይ 225 2.6 በመቶ፣ የደቡብ ኮሪያው ኮስፒ 3 በመቶ እንዲሁም የአውስትራሊያው ኤኤስኤክ 1.9 በመቶ ገበያ ማሽቆልቆሉን አሳይቷል።
- ጂቡቲ በአፋር ክልል በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 8 ሰዎች ሲገደሉ፤ ሌሎች 6 ሰዎች ቆሰሉከ 4 ሰአት በፊት
- ዓለም አቀፉን የእርዳታ ሰንሰለት በቀናት ውስጥ ቀጥ ያደረገው የአሜሪካ ውሳኔከ 6 ሰአት በፊት
- ካናዳ አሜሪካ ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ እንደምትጥል የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ2 የካቲት 2025
ቻይና አዲስ አመቷን እያከበረች የነበረ በመሆኑ ገበያዎቿ ዝግ ሆነው ቆይተዋል።
የአሜሪካው ዶላር ጭማሬ ያሳየ ሲሆን ከቻይናው መገበያያ ገንዘብ ዩዋን ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ብልጫ አሳይቷል።
የካናዳ ዶላር ደግሞ ከአውሮፓውያኑ 2003 ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ወርዷል። “በሁለቱ የዓለም ታላላቅ ምጣኔ ኃብቶች መካከል የተራዘመ የንግድ ጦርነት ሊኖር ይችላል የሚለው ጉዳይ ባለሃብቶችን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል” ሲሉ የኬሲኤም ትሬድ የፋይናንስ ድርጅት ዋና የገበያ ተንታኝ ቲም ዋተረር ያስረዳሉ።
ሌላኛው ተንታኙ የባለ ኃብቶች ስጋት ነው ብለው የጠቀሱት ትራምፕ በቀጣዩ ታሪፍ የሚጥሉባቸው አገራት የትኞቹ ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ነው።
ባለፈው ሳምንት የታወጀው የትራምፕ አስተዳደር ታሪፍ የአሜሪካ ሶስት ታላላቅ የንግድ አጋሮች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ በዚህ እንደማያቆሙ ዝተዋል።
ትራምፕ አሜሪካን በጥሩ መልኩ አላስተናገዳትም ባሉት የአውሮፓ ኅብረት ላይም በቅርቡ ታሪፍ ለመጣል ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
ታሪፍ መጣል ለአሜሪካ ለአጭር ጊዜ ምጣኔ ኃብት ጥቅም ሊያስገኝላት ቢችልም ረዘም ባለ ጊዜ ግን የከፋ አደጋ መደቀናቸውን ሳክሶ የተሰኘው የኢንቨስትመንት ባንክ ከፍተኛ ባለሙያ ቻሩ ቻናና አስጠንቅዋል።
“ታሪፍ ደጋግሞ መጣሉ ሌሎች አገሮች በአሜሪካ ላይ ያላቸውን መተማመን እንዲሸረሸር እና ይህም የዶላርን ዓለም አቀፍ ሚና ያዳክመዋል” ሲሉ አክለዋል።
ትራምፕ ማክሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ ተግባራዊ የሚሆኑትን ታሪፎች በተመለከተ ከካናዳ እና ሜክሲኮ መሪዎች እንደሚነጋገሩ ገልጸዋል።
ሁለቱ አገራት፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ 25 በመቶ እንዲሁም ቻይና 10 በመቶ ታሪፍ ይጣልባቸዋል ተብሏል።