
ከ 5 ሰአት በፊት
የትራምፕ አስተዳደር አብዛኞቹን የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤይድ) ሰራተኞችን አስተዳደራዊ ዕረፍት እንዲወጡ ሲያስገድድ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ አባረረ።
እሁድ ተግባራዊ በሆነው ትዕዛዝ መሰረት 4 ሺህ 200 ሰራተኞች ዕረፍት እንዲወጡ ሲገደዱ፤ ቢያንስ 1 ሺህ 600 ሰራተኞች ተባረዋል።
ይህ ውሳኔ ትራምፕ በሺዎች የሚቆጠሩ የዩኤስ ኤይድ ሰራተኞችን በማባረር ድርጅቱን ለማጠፍ እየወሰዱት ያለው እርምጃ ህጋዊ ተግዳሮት ከገጠመው በኋላ የተከተለ ነው።
የፌደራሉ ፍርድ ቤት ዳኛ አስተዳደሩ የአሜሪካውን የረድኤት ድርጅት ለመበታተን የሚያደርገውን ዕቅድ ቢያስቆምም ሌላ ዳኛ ሰራተኞች አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ ወይም እንዲባረሩ የሚያደርገውን መንገድ ጠርገዋል።
በአውሮፓውያኑ 1961 የተቋቋመው ዩኤስ ኤይድ የቅርቡ ሰራተኞችን የማባረር ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት 10 ሺህ ያህል ሰራተኞች በአሜሪካ ነበሩት።
ወሳኝ ተግባራት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት የተጣለባቸው ወይም አመራር ያሉ ሰራተኞች ይህ አስገዳጅ አስተዳደራዊ ዕረፍት አይመለከታቸውም ተብሏል።
በድርጅቱ ምን ያህል ሰራተኞች እንዲቆዩ ግልጽ ባይሆንም ተቋሙ ከዚህ ቀደም 611 የሚሆኑት ወሳኝ የሚባሉ ተግባራትን የሚሰሩ እንደሆነ አስቀምጦ ነበር።
- ከ10 ዓመት በኋላ ከሐማስ እስር ነጻ የወጣው ቤተ-እስራኤላዊ አቬራ መንግሥቱ ማን ነው?23 የካቲት 2025
- ምዕራባውያንን ያሳሰበው የፑቲን ምሥጢራዊ የጥቃት መሳሪያከ 6 ሰአት በፊት
- ዘለንስኪ ‘ሰላም የሚያመጣ ከሆነ ሥልጣኔን ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ’ አሉከ 5 ሰአት በፊት
Skip podcast promotion and continue reading

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት
ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!
End of podcast promotion
ለሰራተኞቹ በደረሰው በዚህ ኢሜይል በውጭ አገራት ለተሰማሩ እና በፈቃደኝነት ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ አሜሪካዊ የዩኤስኤይድ ሰራተኞች ጉዟቸውን እንደሚደግፍ አስታውቋል። የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ሪፖርት እንዳደረገው ወደ 4 ሺህ 200 የሚጠጉ ሰራተኞች አስተዳደራዊ ዕረፍት ላይ ናቸው።
በዩኤስ ኤይድ ድረ ገጽ መሰረት ተጨማሪ 1 ሺህ 600 ሰራተኞች ቅነሳ እንደሚደረግ አትቷል።
በአጠቃላይ ከዚህ ቀደም አስተዳደራዊ ዕረፍት እንዲወጡ የተደረጉትን ጨምሮ 5 ሺህ 800 የሚሆኑ ሰራተኞች አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወጡ ወይም እንዲባረሩ ተደርገዋል። ይህ አኃዝ ከድርጅቱ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የሰው ኃይል ነው። አርብ ዕለት የዋሽንግተኑ ዳኛ ካርል ኒኮላስ የትራምፕ አስተዳደር የዩኤስኤይድ ሰራተኞችን ለማስወገድ የያዘውን ዕቅድ ወደፊት ሊገፋበት እንደሚችል ብይን አስተላልፈዋል። ባለፈው ሳምንት ሌላ የፌደራል ዳኛ የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካው ምክር ቤት ያጸደቀውን እና መንግሥት በውጭ ዕርዳታ ላይ የሚያደርገውን የገንዘብ ዕርዳታ እንዲቀጥል የሚጠይቀውን ውሳኔ እያከበረ አይደለም ብሎ ነበር።
በአሁኑ ወቅት በአስተዳደራዊ ዕረፍት እንዲወጡ የተደረጉ ሰራተኞች እንደገና ይቀጠራሉ ወይስ የስራ ዘርፋቸው ሊታጠፍ እንደሚችል ግልጽ አይደለም።
የትራምፕ አስተዳደር በቱጃሩ ኤለን መስክ እየመራው ባለው ወጪዎችን ለማዳን የፌደራል መስሪያ ቤቶችን የሰው ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ የሚለውን እየተከለ ይገኛል።
ቅዳሜ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በተካሄደ የወግ አጥባቂዎች ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ “ዩኤስ ኤይድ የተሰኘውን የግራ ክንፍ የማጭበርበሪያ መሳሪያ ውጤታማ በሆነ መንገድ ቀጭተነዋል” ብለዋል።
አክለውም ” የተቋሙ ስም ከቀድሞ ህንጻው እንዲወገድ ተደርጓል እናም ያ ስፍራ የጉምሩክ እና የድንበር ጠባቂ ወኪሎችን የሚይዝ ይሆናል” ሲሉም አስረድተዋል።
በአሜሪካ ስደትን የሚቆጣጠረው የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ መስሪያ ቤት በአገሪቱ መዲና ማዕከል በሚገኘው የዩኤስ ኤይድ ህንጻ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው።