
ከ 4 ሰአት በፊት
በባለፈው መስከረም ወር በእስራኤል ለተገደሉት የሔዝቦላህ መሪ ሐሰን ናስራላህ ቀብር ሽኝት በርካታ ደጋፊዎቻቸው ተገኙ።
በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ዳርቻ ላይ ወደሚገኝ ስታዲየም ጥቁር ልብስ የለበሱ ለቀስተኞች ትናንት እሑድ በብዙ ቁጥር ጎርፈዋል።
ለቀስተኞቹ በቀናት ልዩነት ለተገደሉት የሐሰን ናስረላህ ተተኪ ሐሺም ሰይፈዲንም ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።
ሐሰን ናስራላህ በመካከለኛው ምሥራቅ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር ከቻሉ መንፈሳዊና ወታደራዊ መሪዎች አንዱ ነበሩ።
ይህ የቀብር ሥነ ሥርዓት በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የሔዝቦላህ ሮኬት ማስወንጨፊያዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ ጀምራለች።
በወቅቱ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ያልበገራቸው የናስረላህ ደጋፊዎች 50,000 ሰው በሚይዘው ካሚል ቻሞን ስታዲየም ታጭቀው ነበር።
የሐሰን ናስራላህ አስክሬን በሔዝቦላህ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆ ታይቷል።
በዚህ የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ የሐሰን ናስራላህ የተቀዱ ንግግሮች ለሕዝብ ዕይታ ቀርበዋል።
በርካታ ደጋፊዎቻቸውን በዝማሬ፣ ባንዲራ በማውለብለብ እና የመሪዎቹን ፎቶ ይዘው ይታዩ ነበር።
የወቅቱ የሔዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሴም ካልታወቀ ቦታ በቪዲዮ ሊንክ ለሐዘንተኞች ንግግር ሲያደርጉ ”መቼም ቢሆን ለጠላቶቻችን አንንበረከክም”ብለዋል።
አንድ የ55 ዓመቷ ኡም ማህዲ የተባሉ ሐዘንተኛ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የቀብር ሥነ ሥርዓቱ “እዚህ መገኘታችን ለዓላማው ሲል ሁሉንም ነገር ለተወው ለታላቁ መሪያችን ናስራላህ ልናደርገው ከምንችለው በጣም ትንሹ ነገር ነው” ብለዋል።
ሐሰን ናስራላህ በእስራኤል ሊገደሉ እንደሚችሉ በመስጋት ለዓመታት በአደባባይ ሳይታዩ ቆይተዋል።
ሟቹ መሪ ከኢራን ጋር የጠበቀ ግላዊ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ሔዝቦላህን ወደ ፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይል በማሸጋገር ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።
- ከ10 ዓመት በኋላ ከሐማስ እስር ነጻ የወጣው ቤተ-እስራኤላዊ አቬራ መንግሥቱ ማን ነው?23 የካቲት 2025
- ምዕራባውያንን ያሳሰበው የፑቲን ምሥጢራዊ የጥቃት መሳሪያከ 6 ሰአት በፊት
- ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?22 የካቲት 2025
Skip podcast promotion and continue reading

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት
ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!
End of podcast promotion
በሐሰን ናስራላህ የ30 ዓመታት አመራር በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች ሀገራት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሔዝቦላህ፣ ከፍልስጤም ታጣቂ ቡድን የሐማስ ተዋጊዎችን እንዲሁም ኢራቅ እና የመን ውስጥ ያሉ ሚሊሻዎችን በማሰልጠን እና ሚሳኤሎችን እና ሮኬቶችን ከኢራን በማግኘቱ በቀጠናው ኃያል ተደርጎ ይታይ ነበር።
አሁን ግን ይህ ጥንካሬው የሟሸሸ ይመስላል።
ሐሰን ናስራላህ የተገደሉት ዳሂድ በተባለ የቤይሩት ሰፈር ነው። ይህ ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለት የነበረው አካባቢ ከናስራላህ ሞት በኋላ ለሐዘንተኞች ክፍት ሆኗል።
ሐሰን ናስራላህ በ64 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
በዚህ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ወቅት የእስራኤል ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሲያንዣብቡ ነበር።
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር በኤክስ ሰሌዳቸው ላይ እንደፃፉት ”የእስራኤል አውሮፕላኖች በስታዲየሙ ላይ እየበረሩ የነበረው ለሐዘንተኞቹ ግልፅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው። እስራኤልን ለማጥፋት የሚያስፈራራ ሁሉ መጨረሻቸው ይህ ነው።”
የእስራኤል ሊባኖስ ወረራ የተከሰተው በጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው።
እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 2024 በእስራኤል የተሰሩ የ’ዎኪ ቶኪዎች’ ድንገተኛ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገድለዋል ።
ከእስራኤል ጋር በተፈጠረ ግጭት ብዙዎቹ የሔዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖለቲካ መሪዎች ተገድለዋል።
ጥቃቱ በሊባኖስ ወደ 4,000 የሚጠጉ ሰዎችን ገድሏል። በኅዳር ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ከመደረጉ በፊት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ።
በትናንቱ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢራን፣ ኢራቅ እና የመን ተወካዮች ተገኝተዋል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ ሟቾቹን “ጀግኖች” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።