
ከ 6 ሰአት በፊት
1.4 ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር ያላት ህንድ አንድ ቢሊዮን የሚሆነው ሕዝቧ ሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን ለመግዛት ገንዘብ እንደሌለው አንድ ሪፖርት አመለከተ።
የመግዛት አቅም አለው የተባለው የአገሪቱ ሸማች የማኅበረሰብ ክፍል ከሜክሲኮ የሕዝብ ቁጥር በመስተካከል ከ130 እስከ 140 ሚሊዮን የሚሆነው ብቻ እንደሆነ ብሉም ቬንቸርስ የተባለ ገንዘብ ተቋም ሪፖርት ገልጿል።
ሪፖርቱ ተጨማሪ 300 ሚሊዮን የሚሆኑ የህንድ ዜጎች አዲስ ወይም ፍላጎት ያላቸው ሸማቾች ቢሆኑም የገንዘብ ቦርሳቸውን ለመክፈት ግን ያመነታሉ ብሏል።
የእስያ ሦስተኛ ግዙፉ ምጣኔ ሀብት ባለቤት በሆነችው ህንድ ሸማቹ የማኅበረሰብ ክፍል የማሽቆልቆሉን ያህል የሸማቹ ቁጥር እየሰፋ አለመሆኑንም ጠቁሟል።
ይህም ማለት የህንድ ባለፀጋዎች ሀብታቸው እያደገ ቢሆንም ከበርቴው ሕዝብ ግን በቁጥር እያደገ አይደለም ማለት ነው።
የአገሪቱ ሸማች የማኅበረሰብ ክፍል በልዩ ሁኔታ እየተቀረፀ ሲሆን፤ በተለይም ቅንጡ ምርቶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች ለሰፊው ገበያ ከማቅረብ ይልቅ ለጥቂት ሰዎች በልዩነት እንዲያቀርቡ አድርጓል።
ይህም እጅግ ቅንጡ በሆኑ ቤቶች እና ለጥቂቶች ብቻ ተብለው በሚሰሩ ስልኮች ሽያጭ እየታየ ነው።
ለአብዛኛው ማኅበረሰብ ኪስ በሚመጥን ገበያ ላይ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት 40 በመቶ ወደ 18 በመቶ አሽቆልቁሏል።
- በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ካናዳዊያን የኢላን መስክ ዜግነት እንዲነጠቅ ፊርማ እያሰባሰቡ ነውከ 9 ሰአት በፊት
- የኳታር አየር መንገድ ከጥንድ ተጓዦች አጠገብ ሬሳ በማስቀመጡ ይቅርታ ጠየቀከ 8 ሰአት በፊት
- የዩክሬን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር የማዕድን ስምምነት ማድረጋቸውን አስታወቁከ 9 ሰአት በፊት
በህንድ በንግድ ምልክታቸው የሚታወቁ እና ‘ብራንድ’ የሚባሉ ምርቶች ገበያው ላይ ትልቅ ድርሻ እያገኙ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ድምፃዊያን ለሙዚቃ ኮንሰርቶቻቸው ትኬቶችን በውድ እሸጡ ነው።
ከሪፖርቱ ፀሐፊዎች አንዱ የሆኑት ሳጂት ፓይ አዝማሚያውን እየተከተሉ ያሉ ኩባንያዎች ትርፋማ እየሆኑ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሰፊው ገበያ ላይ የሚያተኩሩ ወይም ምርቶችን በልዩነት የማያቀርቡ ኩባንያዎች ከገበያው ድርሻቸውን እንዳጡም ተናግረዋል።
የሪፖርቱ ውጤት በህንድ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ ከበርቴዎች የበለጠ ሀብታም ሲሆኑ ደሃዎች ደግሞ የመግዛት አቅማቸው መዳከሙን በድጋሚ የመሰከረ ነው።
ከወረርሽኙ በፊት ይህ የተለያየ ሲሆን፤ የህንድ የሀብት ክፍፍል ልዩነት የሰፋ ስለመሆኑ ይናገራል።
10 በመቶ የሚሆኑ ህንዳዊያን 57.7 በመቶውን የአገሪቱን ብሔራዊ ሀብት ይዘዋል። ይህ አሀዝ እ.አ.አ በ1990 34 በመቶ ነበር።
ከ50 በመቶ በታች የሆነው የህንድ ሕዝብ ከአገሪቱ ሀብት ድርሻው ከ22.2 በመቶው ወደ 15 በመቶ አሽቆልቁሏል።
አዲሱ ሪፖርት ይህን ማሽቆልቆሉን ከማሳየት ባለፈ ችግሩ ስር የሰደደ መሆኑን ጠቁሟል።
የመግዛት አቅም ዝቅ ማለቱ ብቻም ሳይሆን ቁጠባ ሲያሽቆለቁል በአብዛኛው ህዝብ ላይ እዳ ማሻቀቡን አሳይቷል።