Mengistu Musie

የተባበሩት የሳህል ግዛቶች

ቡርኪና ፋሶ፣ ኒጀር እና ማሊ ኮንፌደሬሽን

====================

በ1961 ከኤርትራ የመገንጠል ንቅናቄ የጀመረው የብሔር ፖለቲካ ሦስት ሽህ አመት የዘለቀ civilization እንዲፈርስ እና በአፍሪካ ቀንድ ትንንሽ መንግስታት እንዲፈጠሩ በሚሰብክበት በዚህ ዘመን፡፡ ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነጻ የወጡት ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ እና ኒጀር በ2023 በተስማሙት መሰረት በ2024 The Alliance of Sahil State (AES) የተባለ አዲስ ኮንፌደሬት መንግስት እና ሐገር መስርተዋል፡፡ ይህ ጅማሮ ለሦስቱ ሀገራት ወደአንድ መምጣት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የአንድ ታላቅ ሐገር የመሆን ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ሁሉ ለፓን አፍሪካ ህልም፡፡ አፍሪካን አንድ የማድረጉ ሀሳብ ትልቅ እርምጃ ወደፊት የታየበት ተስፋ ነው፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ ደግሞ እንዲህ አይነት ዜና በሚሰማበት በዚህ ዘመን የቀደምቷ ስልጡን የአፍሪካ ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ ኦነግ/ህወሓት/በሚባሉ ጸረ አንድነት ሐይሎች የምትታመስበት እና የሶስት ሽህ ዘመን መንግስታዊ እና ሀገራዊ ታሪኳ አደጋላይ የወደቀበት ግዜ ነው፡፡

ዛሬ ከልሂቅ እስከደቂቅ በመንደር የሚያስቡ ምሁራን በሚርመሰመሱባት ኢትዮጵያ አፍሪካን አንድ ለማድረግ የሚሰሩ ሊቆች ከቅኝ ግዛት ነጻ በወጡ ሐገሮች መፈጠራቸው ለአውሮፓ ቅኝ ገዥወች ስጋት፤ ለአፍሪካ ተስፋ ጥሏል፡፡ ልክ እንደአውሮፓ ቅኝ ገዥወች የህሊና ሰለባ የሆኑት የኢትዮጵያ የኦነግ/ህወሓት ልሂቃንም የአዲሱን የሳህል አንድነት መንግስት እንደጠላት የሚቆጥሩ እና Self-determination up to and including secession የሚሉትን የምእራብ neocolonialists የሰጧቸውን መፈክር ይዘው ከአንድ ጦርነት ወደሌላ የሚዘጋጁ ጸረ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ጸረ አፍሪካ የሆኑ ኦነጋውያን ህወሓቶችንም በምድራችን በዚህች የትናንት የአፍሪካ እና የአለም ጥቁር ሕዝቦች ኩራት በተባለች ሐገራችን ይርመሰመሳሉ፡፡

የዚህች የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት ሐገር (ኢትዮጵያ)ን የሚገዛው ዘረኛ መንግስት በዘር የተለዩትን ኢትዮጵያውያን ከምድረ ገጽ አጠፋለሁ የኦሮሞን ግዛት አሰፋለሁ በሚል ቅዠት ድሮን በመግዛት ሌት ተቀን ንጹሀንን የሚገድል መንግስት የተፈጠረበት ዘመን ሆነን የአፍሪካ ኮንፌደሬሽንን ጅማሮ ስናይ በሐገራችን ውድቀት ተስፋ የቆረጥነውን ያህል፤ በአፍሪካውያን ወደአንድ ለመምጣት የሚያደርጉትን ትጋት በማየት የጨለመ ተስፋችንን አለምልመውታል፡፡