
ከ 5 ሰአት በፊት
በደቡብ ኮሪያ ተዋጊ ጄቶች በስህተት ስምንት ቦምቦች በመኖሪያ ስፍራዎች መጣላቸውን ተከትሎ 15 ሰዎች መጎዳታቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ከተጎዱትም መካከል ሁለቱ በጠና መሆኑ ተገልጿል።
ተዋጊ ጄቶቹ ሐሙስ ዕለት የተኩስ ልውውጥን ያካተተ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ በነበረበት ወቅት ይህ ክስተት ተፈጥሯል ተብሏል።
በሰሜን ኮሪያ አቅራቢያ ፓቺዮ ከተማ ኬኤፍ-16 የተሰኙ አውሮፕላኖች ሲያደርጉት የነበረው፤ ከሰሜን ኮሪያ ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ለመከላከል ያለውን ዝግጁነት የሚፈትሹ መደበኛ ልምምዶች አካል እንደሆነም ተገልጿል።
የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል ድርጊቱ ላይ ምርመራ መክፈቱን እንዲሁም ለደረሰው ጉዳት ይቀርታ ጠይቆ ለተጎዱት ካሳ እንደሚከፍል አስታውቋል።
ከልምምዶች የሚወነጨፉ ጥይቶች አንዳንድ ጊዜ በመኖሪያ ቤቶች አቅራቢያ ቢያርፉም፣ ብዙም ጉዳት አያስከትሉም።
ሁለት ግለሰቦች አንገታቸው እና ትከሻቸው ላይ ስብራት እንደደረሰባቸው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ፍንዳታው በተከተሰበት ወቅት በስፍራው መኪና እየነዱ የነበሩ የ60 ዓመት አዛውንት አንገታቸው ላይ ፍንጣሪ መሰካቱን ዮንሃፕ ለተሰኘው የአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።
“መኪና እየነዳሁ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ፍንዳታ ሰማሁ። ከእንቅልፌ ስነቃ አምቡላንስ ውስጥ ነበርኩ” ብለዋል።
- “‘ቁርጭምጭሚት’ የሚለው ቃል ያስቀኛል” ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬከ 6 ሰአት በፊት
- “ኬንያ ለመጪው የዓለም ዋንጫ በማለፍ ብዙዎችን ማስደነቅ ትችላለች” አዲሱ አሠልጣኝ ቤኒ ማካርቲከ 6 ሰአት በፊት
- የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ጄኔራል መታሰር የሰላም ስምምነቱን የሚጥስ እንደሆነ ተገለጸ6 መጋቢት 2025
“ኬኤፍ ተዋጊ ጄታችን ኤምኬ 82 የተሰኙ ስምንት ቦምቦችን ባልተለመደ ሁኔታ ጥሏል። ቦምቦቹም ከልምምድ ቀጣና ውጪ አርፈዋል” ሲል የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል ለቢቢሲ በላከው መግለጫ አትቷል።
የአንደኛው ጄት አብራሪ የተሳሳቱ መዳረሻዎችን በማስገባቱ ቦምቦቹ በመኖሪያ ስፍራዎች ውስጥ እንዲወድቁ ምክንያት መሆኑን የአገሪቱ መከላከያ አትቷል።
መርማሪዎች ሁለተኛው ጄት ለምን ቦምቡን እንደጣለ እንዳልደረሱበት የገለጸው መከላከያው ማንኛውም የተኩስ ልውውጥን ያካተቱ ልምምዶች እንደሚቆሙ ገልጿል።
ከነዋሪዎች በተጨማሪ አንድ የቤተ ክርስቲያን ህንጻ እና መኖሪያ ቤቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ይፋ የሆኑ ምስሎች መስኮቱ የተሰበረ ህንጻ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ጣሪያ ጉዳት መድረሱን አሳይተዋል።
በወቅቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ቴሌቪዥን ሲመለከቱ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪ የሰሙት ፍንዳታ ቤቱን እንዳናወጠ እና እንደ “ነጎድጓድም” ነበር ሲሉ ነው ለዮንሃፕ የተናገሩት።
በአቅራቢያው የሚገኝ የአረጋዊያን እንክብካቤ ማዕከል ዳይሬክተር በበኩላቸው የማዕከሉ ሕንፃ መስኮቶች ተሰባብረው አንድ አስተማሪያቸው እንደቆሰሉ እና ወደ ህክምና ማዕከል ተወስደዋል ብለዋል።
አረጋውያን ባይጎዱም “በጣም ከመፍራታቸው የተነሳ ሁሉንም ወደ ቤት ላክናቸው” ሲሉ ገልጸዋል።
የፖቾን ግዛት ባለስልጣናት ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ተደርገው የፈንጅ አስወጋጅ ቡድን ያልፈነዱ ቦምቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማስወገድ ሲሰሩ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ነገር ግን ምንም ያልፈነዱ ቦምቦች በስፍራው ላይ እንዳላገኙ ባለስልጣናቱ መናገራቸውን ዮንሃፕ ዘግቧል።
ሐሙስ እለት ሲካሄድ የነበረው ስልጠና ከአሜሪካ ኃይሎች ጋር በጋራ ሲደረግ የነበረ ልምምድ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።