
Mengistu Musie
የአብይ አህመድ የባህር ወደብ ፕሮፖጋንዳ ባዶነት
======================
የአብይ አህመድ ፕሮፖጋንዳ መረብ እና የዲጅታል ሰራዊቱ እስከ ወዶ ገብ ግለኞች በአማራ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ ሰላማዊ ዜጎችን በየቀኑ የመግደል ጀኖሳይዳል ጦርነትን ለማለባበስ በየግዜው ወደማህበራዊ ሚዲያ የሚገፋው ፕሮፖጋንዳ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ ምናልባት ለአንድ አመት ግዜ ከሶማሌ ላንድ ጋር ውል ፈጸምን በሚል እና የባሕር በር ተገኘ ብለው አረፋ ሲደፍቁ ይውሉ የነበር ፕሮፖጋንዲቶችን አይተናል፡፡ የሶማሌ ላንድ እና የባህር በሩ ጉዳይ ከ 50 አመታት ውል ወደ ስድስት ወር ግርግር ተለወጠ እና የቀኝ ኋላ ዞሮ አረመኔው በሰሞኑ ከሶማልያ ጋር እፍ ያለ ፍቅር እና የጫጉላ ግዜ ላይ ናቸው፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የሚዲያ ሰራዊቱን አሰልፎ እና በእራሱ በሚያስተዳድራቸው ሚዲያወች በአንድ በኩል ጨምሮ የባሕርበር አስፈላጊነት ሲሰበክ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ጦር ልትሰብቅ ነው!! አሰብን ለመውሰድ እየተዘጋጀን ነው በሚል ያው ተከፋዩ ካድሬ ሲጮሕ ይውላል፡፡ እውነታው ግን የአብይ አህመድ ሰራዊት ላለፉት አመታት በከፈተው የውጥ ጦርነት ከታች ላይ እየባዘነ ያለበት እና ቁመናውም ለከፍተኛ ኮንቬንሽናል ግጭት ብቁ አለመሆኑ እየታወቀ ክድሬው የሌለውን አቅም አጉልቶ ሱያ ሲያወናብድበት በዝምታ ሊታለፉ አይገባም፡፡
በአፍሪካ ቀንድ በተለይ በውጭ ሓይሎች ተቀጥረው የሚሰሩት መሪወች ሰላም ለሕዝባችን ቢሰጡ ወደብ የማግኘቱ ጉዳይ በዲፕሎማሲ እና በመልካም ግንኙነት ሊፈታ የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ በምእራብ አፍሪካ በሦስት ሀገራት ኮንፌደሬሽን የተጀመረው ትንንሽ ሀገራትን በአንድ እና በሰላም ማገናኘት በአፍሪካ ቀንድ የበለጠ ሊተገበር የሚገባው እና በሳል መሪወችን ስራ እና ተግባር የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡ የአፍሪካ ቀንድ ለምእራብ ጅኦፖለቲካ ባላንስ እና ለጥቅማቸው መሳሪያ የሆኑትን እንደ አብይ አህመድ ያሉ አረመኔወችን ማስወገድ የቅድሚያ ተግባር ሊሆን እንጅ ሉ’አላዊ ሐገራት ላይ መዝመት ቅድሚያ የሚሰጠው የግዜው ጉዳይ አይደለም፡፡ የአብይን እና ጄሌወቹን የፕሮፖጋንዳ ቱሪናፋ ትቶ ይህን ዘረኛ ስርአት ማስወገድ እንጅ በነሱ የሀሰት ዜና እና ወሬ መጠመድ ተገቢ አይድለም፡፡