
ከ 2 ሰአት በፊት
ለሰሜን ኮሪያ አገዛዝ እንደሚሰሩ የሚታመኑ መረጃ መንታፊዎች ከዘረፉት 1.5 ቢሊዮን ዶላር የበይነ መረብ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) 300 ሚሊዮን ዶላሩን በጥሬ ማውጣታቸው ተነግሯል።
ላዝረስ ቡድን እየተባሉ የሚጠሩት መንታፊዎች ከሁለት ሳምንት በፊት ባይባይት ከተባለ የበይነ ገንዘብ ኩባንያ ትልቅ የዲጂታል ገንዘብ መዝረፋቸው ታውቋል።
ባለፈው የካቲት 14 ወንጀለኞች ከባይባይትን አቅራቢ በሚስጥር የገንዘብ ዝውውሩን በመመንተፍ ድርጅቱ ወደራሱ ቦርሳ የላከ መስሎት ወደ መንታፊዎቹ ልኳል።
የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ቤን ዙ ገንዘቡ እንዳልተወሰደ ለደንበኞቻቸው ማረጋገጫ ሰጥተው ነበር።
ዘረፋው ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ መረጃ መንታፊዎቹ ጥሬ ገንዘቡን አውጥተው መጠቀም እንዳይችሉ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቷል።
የዘርፉ ባለሙያዎች ቡድኑ ገንዘቡን ለሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ለመከላከያ ልማት ለማስገባት ሌት ከቀን እንደሚሰራ ይናገራሉ።
በበይነ ገንዘብ ዝርፊያ ከሚታወቁ መንታፊዎች መካከል የሰሜን ኮሪያዎቹ ገንዘቡን በማጠብም ወደር የላቸውም ይላሉ።
አሜሪካ እና አጋሮቿ በቅርብ ዓመታት በርካታ መረጃዎችን በመመንተፍ ሰሜን ኮሪያ ለወታደራዊ እና የኒውክሌር ልማቷ ታውላለች በሚል ይከሳሉ።
ከባይባይት ከተዘረፈው ገንዘብ 20 በመቶው የገባበት ባለመታወቁ መመለስ እንደማይችል ድርጅቱ እና መርማሪዎች ተናግረዋል።
- የካናዳ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሜሪካ ጋር የተጀመረውን የንግድ ጦርነት ለማሸነፍ ቃል ገቡከ 2 ሰአት በፊት
- በትራምፕ የካቢኔ ስብሰባ በኢላን መስክ ላይ የተነሳው ቅሬታ እና የተሰጠው ሥልጣን መቀነስከ 4 ሰአት በፊት
- እስራኤል የመላ ጋዛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲቋረጥ አዘዘችከ 3 ሰአት በፊት
Skip podcast promotion and continue reading

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት
ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!
End of podcast promotion
ድርጅቱ ከዝርፊያው በኋላ የተዘረፈውን ገንዘብ ብድር ወስዶ መተካቱን የገለፀ ሲሆን፤ ላዝረስ ቡድን ላይም ጦርነት ማወጁን አስታውቋል።
መንታፊዎቹ የዘረፉትን በይነ ገንዘብ በሚታወቁ ማስተላለፊያ አገልግሎቶች እንደ ዶላር በመሰሉ መደበኛ ገንዘቦች ለመቀየር ከሞከሩ ገንዘቡን መያዝ ይቻላል።
እስካሁን በዚህ መንገድ 20 የሚሆኑ ሰዎች 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ በይነ ገንዘብ እንዳይተላለፍ ቢያግዱም፤ ባለሞያዎች ግን የቀረውን ገዘንዘብ ለማስመለስ እምብዛም ተስፋ አይታያቸውም።
ሰሜን ኮሪያ ካላት የምንተፋ እና የገንዘብ ማጠብ ብቃት አንፃር የቀረውን ገንዘብ ለማስመለስ ያለው እድል አነስተኛ ነው ይላሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ዝውውሩን ተከታትሎ ለማገድ ሁሉም የበይነ ገንዘብ ኩባንያዎች ተባባሪ አለመሆን የተዘረፈውን ገንዘብ ለማስመለስ እንደ ችግር ታይቷል።
ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ላዝረስ ከተባለው ቡድን ጀርባ እንዳለች አምና የማታውቅ ሲሆን፤ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል ግዙፍ መረጃ በመመንተፍ በመላው ዓለም ስሟ የሚጠቀስ ብቸኛዋ አገር ናት።
ከዚህ ቀደም ቡድኑ ባንኮችን ኢላማ የሚያደርግ ሲሆን፤ ባለፉት አምስት ዓመታት ግን የበይነ ገንዘብ ኩባንያዎችን ማጥቃት ላይ አተኩሯል።
ዘርፉ እምብዛም ቁጥጥር የማይደረግበት እና የተመዘበረን ገንዘብ ለማስመለስ ጥቂት አማራጭ መንገዶች ብቻ ያሉት ነው።
በቅርብ ጊዜ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተያያዙ አራት ምንተፋዎች ያሉ ሲሆን እ.አ.አ በ2023 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የበይነ ገንዘብ ተዘርፏል።
በ2020 አሜሪካ የላዝረስ ቡድን አካል በመሆን ሰሜን ኮሪያዊያዊያንን በአስቸኳይ ከሚፈለጉ ወንጀለኞች ዝርዝር ውስጥ አስገብታለች።
ነገር ግን ግለሰቦቹ ሰሜን ኮሪያን ለቀው ካልወጡ በስተቀር በቁጥጥር ስር የማዋላቸው እድል እጅግ ዝቅተኛ ነው።