
ከ 1 ሰአት በፊት
ለ20 ዓመታት ያህል በእንጀራ እናቱ ታግቶ የነበረው አሜሪካዊ የተያዘበት ክፍል ላይ እሳት በመለኮስ ማምለጡን ባለስልጣናቱ ተናገሩ።
ቃጠሎውን ተከትሎ የመጡ ባለስልጣናት በጠባብ ክፍል ታግቶ ነበረውን የ32 ዓመቱ ግለሰብ መታደጋቸውም ተነግሯል።
ታግቶ የነበረው ግለሰብ 30 ኪሎግራም የሚመዝን ሲሆን በቃጠሎው የገባበት ጭስም በሆስፒታል ህክምና ተደርጎለታል።
ግለሰቡ ለዓመታት ያህል “ተደጋጋሚ ጥቃት፣ ረሃብ፣ ቸልተኝነት እና ኢሰብዓዊ ድርጊቶች” ከደረሱበት በኋላ እሳት መለሰኮሱን ማመኑን የኮነቲኬት ግዛት ፖሊስ ገልጿል።
ልጇን አግታ አስርባዋለች የተባለችው ግለሰብ በአፈና እና በጭካኔያዊ ተግባር ክስ ቀርቦበታል። ግለሰቧ ክሱን አስተባብላለች።
ግለሰቡ እሳት የለኮሰበትን ምክንያት ሲገልጽ “ነጻነቴን ፈልጌ ነው” ሲል ለፖሊስ ተናግሯል።
የእንጀራ እናቱ በቀን አንድ ሳንድዊች ምግብ እና ሁለት ትናንሽ የውሃ ጠርሙሶች ለዓመታት ትሰጠው እንደነበር አቃቤ ህግ ገልጿል።
የቤት ውስጥ ስራዎችን ለመስራት በቀን ለሁለት ሰዓታት ከነበረበት እገታ ነጻ እንዲወጣ ቢደረግም የእንጀራ እናቱ ቁጥጥር አይለየውም ተብሏል።
ግለበሰቡ ሊሞት እንደሚችል እያወቀ የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘር)፣ ወረቀት እና መለኮሻ (ላይተር) በመጠቀም እሳት ማስነሳቱን አቃቤ ህግ ረቡዕ በዋለው ችሎት ላይ አስረድቷል።
የ56 ዓመት የሆነችው የእንጀራ እናቱ ኪምበርሊ ሱሊቫን እሳቱ በተነሳበት ወቅት ቤት ውስጥ የነበረች ቢሆንም ባለስልጣናት በስፍራው ሲደርሱ እንዳላነጋገረቻቸው ተገልጿል።
- በመቀለ ትናንት የተከሰቱ ዐበይት ክንውኖች ምንድን ናቸው?ከ 1 ሰአት በፊት
- ፑቲን ከዩክሬን ጋር ለሚደረግ የተኩስ አቁም ከበድ ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጡከ 3 ሰአት በፊት
- በእሳት ከተያያዘው የአሜሪካው አውሮፕላን በክንፉ በኩል መንገደኞችን ማስወጣት ተቻለከ 1 ሰአት በፊት
የተከሳሿ ጠበቃ በደንበኛቸው ላይ የቀረበው ክስ ሐሰት ነው ብለዋል።
“አንድ ክፍል ውስጥ አልተቆለፈም ነበር። በምንም መንገድ አልከለከለችውም። ምግብ ታቀርብለት ነበር። መጠለያ ሰጥታዋለች። በነዚህ ውንጀላዎች አዝናለች” ሲሉ የተከሳሿ ጠበቃ ኢዮያኒስ ካሎይድስ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
እሳቱ የተነሳው ባለፈው ወር ሰኞ የካቲት 10 ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላም ባለስልጣናቱ ግለሰቧን በቁጥጥር ስር አውለዋታል።
የግዛቲቷ ፖሊስ ኃላፊ ፈርናንዶ ስፓኞሎ ጉዳዪን “ልብ የሚሰብር እና የማይታሰብ” ሲሉ ፈርጀውታል።
ተጎጂው ከ11 ዓመቱ ጀምሮ በቤተሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ታግቶ እንደሚገኝ መናገሩን ፖሊስ ገልጿል።
“ለ20 ዓመታት በአንድ ክፍል ውስጥ ተዘግቶበት ነበር፤ ለ20 ዓመታት ያህልም ከዚያች ክፍል ለመውጣት ሲሞክር ነበር” ሲሉ አቃቤ ህግ ተናግረዋል።
ባለስልጣናቱ የታጋቹ ግለሰብ አባቱ መቼ እንደሞተ ግልጽ ባይሆንላቸውም በዚህ ምክንያት ሁኔታው መባባሱን ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ በተገኙበት ወቅት ክብደት ከቁመት አንጻር በሚያሰላው፣ ቢኤምአይ መሰረት 11 መሆኑ ተገልጿል። የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ጤናማ የሚለው ቢኤምአይ ከ18.5 እስከ 24.9 ያለውን ነው።
ስሙ ይፋ ያልሆነው ይህ ግለሰብ በነዚህ ዓመታት ውስጥ ምንም አይነት ህክምና አለማግኘቱን ፖሊስ ገልጿል።