
16 መጋቢት 2025, 08:22 EAT
ዩናይትድ ስቴትስ በዋሺንግተን የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዝደንት ያሰናበተች ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አምባሳደሩ “ዘር ላይ የሚያተኩሩ ፖለቲከኛ ናቸው” ሲሉ ወቅሰዋል።
ኤክስ ላይ መልዕክታቸውን ያሰፈሩት ሩቢዮ የደቡብ አፍሪካው አምባሳደር ኢብራሒም ራሱል አሜሪካ እና ዶናልድ ትራምፕ ጠል ናቸው ብለዋል።
አክለው አምባሳደሩ “ከዚህ በኋላ ወደ ታላቋ ሀገራችን መምጣት አይችሉም” የሚል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን “የሚያስቆጭ” ብሎት ከአሜሪካ ጋር የጋራ ጠቀሜታ ላይ የተመሠረተውን ግንኙነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ በደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኘኑት መሻከር ጀምሯል።
ምንም እንኳ ዝቅተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው ዲፕሎማቶች ከሀገር መባረራቸው አዲስ ዜና ባይሆንም አሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ከሀገራ ስታባርር መስማት የተለመደ አይደለም።
በቅርቡ የደቡብ አፍሪካው አምባሳደር በበይነ መረብ በሰጡት ትምህርት ላይ ስለትራምፕ አስተዳደር የተናገሯቸውን ነገሮች አነጋጋሪ ሆነዋል።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኤክስ ገፃቸው ይህ መሠረት አድርጎ የተፃፈ የቀኝ ዘመም ድረ-ገፅ ፅሑፍ አጋርተዋል።
አምባሳደሩ ትራምፕ “የአንድ ዘር የበላይነትን እያስፋፉ ነው” ሲሉ ይወቅሳሉ፤ አክለው ፕሬዝደንቱ “ነጮች ተበድለዋል የሚለውን ሐሳብ እያንፀባረቁ ነው” ይላሉ።
- ከአሜሪካ የመባረር አደጋ ላይ ያሉ ስደተኞችን የምትረዳው ቀይዋ ካርድ16 መጋቢት 2025
- በበረራ ወቅት ተሳፋሪ ቢሞት ምን ይደረጋል?16 መጋቢት 2025
- የትግራይ ክልል ቀውስ፡ ከፕሪቶሪያ ወዲህ መቼ ምን ተከሰተ?15 መጋቢት 2025

Skip podcast promotion and continue reading

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት
ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!
End of podcast promotion
“የአሜሪካን የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ስንመለከት፤ ‘ማጋ’ የተባለው እንቅስቃሴ የአንድ ዘር የበላይነትን ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን በአሜሪካ ነጮች 48 በመቶ ይሆናሉ የሚለውን ትንበያ ለመመከት የተወጠነ ነው” ብለዋል።
አምባሳደሩ እንደሚሉት ደቡብ አፍሪካ ጥቃት እየደረሰባት ያለው “የአንድ ዘር የበላይነት ጉዳይን በተለመከተ ታሪካዊ ምሳሌ ስለሆንን ነው” ሲሉም ያብራራሉ።
ለዚህ ምላሽ የሰጡት ሩቢዮ አምበሳደር ራሱል “ፐርሶና ነን ግራታ” አሊያም “ተቀባይነት የሌላቸው ግለሰብ ናቸው” ብለዋል።
ባለፈው ወር ትራምፕ ይፋ ያደረጉት መመሪያ ዩናይትድ ስቴትስ ለደቡብ አፍሪካ የምታደርገው እርዳታ እንዲቋረጥ ያዛል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ እየደረሰ ያለው “ፍትሐዊ ያልሆነ የዘር መድልዎ ነው” ይላል።
የደቡብ አፍሪካ ነጭ ዜጎች በአብዛኛው በ17ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ሀገሪቱ ከመጡ ደች ሰፋሪዎች ዘራቸው የሚመዘዝ ነው።
በቅርቡ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ያፀደቀው ሕግ መንግሥት ከነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን ላይ መሬት በግዴታ ለመንጠቅ ያቀደ ነው የሚል ቅሬታ ይሰማል።
“ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ አጥፊዎችን መደገፏን የምትቀጥል እና አናሳ ገበሬዎች ላይ ጥቃት ማድረሷን የማታቆም ከሆነ አሜሪካ የምታደርገውን ድጋፍ ታቋርጣለች” ይላል ዋይት ሐውስ በወቅቱ ያወጣው መግለጫ።
በደቡብ አፍሪካ በአውሮፓውያኑ 2022 የተሠራው የሕዝብ ቆጠራ አፍሪካነርስ የሚባሉትን ነጮች ጨምሮ በአጠቃላይ የነጭ ዜጎች ቁጥር ከአጠቃላይ ሕዝቡ 7.2 በመቶ ነው ይላል።
ቢሆንም በ2018 መንግሥት ያወጣው መረጃ 72 በመቶ የሚሆነው የእርሻ መሬት በነጭ ገበሬዎች እንደተያዘ ያሳያል።
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት መሬት ከገበሬዎች የሚወስደው ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል ከታሰብ ብቻ መሆኑን አሳውቆ ለገበሬዎች ካሳ እንደሚከፍልም ገልጿል።
አምባሳደር ራሱል ከዚህ ቀደም ከአውሮፓውያኑ 2010-2015 በአሜሪካ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
በአፓርታይ ዘመን በልጅነታቸው ኬፕ ታውን የነጮች ነው ተብሎ በታወጀ ወቅት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
ራሱል በዋሺንግተን የፕሪቶሪያ አምባሳደር ሆነው ድጋሚ የተሾሙት ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2024 ነበር።