የሰውነት ሴሎች

18 መጋቢት 2025, 07:02 EAT

የአይረን (ብረት) ንጥረ ነገር እጥረት በዓለም በሰዎች ላይ ለሚከሰት የአካል ጉዳት መንስኤዎች መካከል አንዱ ነው። ነገር ግን እጥረቱ መቼ ችግር እንደሚሆን እና ለማከም ጥሩ የሆነው መንገድ ግልፅ አይደለም።

ሜገን ራየን የድካም ስሜት ሲሰማት ምንም አልመሰላትም ነበር።

የሦስት ዓመት ልጇን ብቻዋን የምታሳድግ እና የሙሉ ጊዜ ሠራተኛ በመሆኗ ድካም እንግዳ ነገር አልመሰላትም ነበር።

በየቀኑ ልጇን ከሕፃናት ማቆያ ለማምጣት ስትሄድ ከልጇ ጋር እንቅልፍ ይወስዳታል።

እንግዳ ነገር ነው ብላ አላሰበችም ነበር። “ይህ እናትነት ነው ብዬ ነበር ያሰብኩት” ትላለች በአሜሪካ፣ ከኒው ዮርክ ከተማ ወጣ ብላ የምትኖረው ሜገን።

ሰኔ 2023 በመደበኛ የጤና ምርመራ ወቅት ሐኪሟ ድካም ይሰማት ከሆነ ጠየቀቻት።

የደም ምርመራ ውጤቷም ሜገን የብረት ወይም የአይረን እጥረት እና ደም ማነስ እንዳለባት አረጋገጠ።

ወደ ኋላ መለስ ብላ ስታስብ ሌሎች ምልክቶችም ነበሩ። በመደበኛነት አካላዊ እንቅስቃሴ ብታደርግም የእግር ጉዞዎች ላይ ለመተንፈስ ትቸገራለች። በእርግዝናዋ ወቅት የብረት እጥረት ገጥሟት ነበር።

አሁን ላይ በዓለም የብረት እጥረት በጣም የተለመደ የንጥረ ነገር እጥረት ነው። ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ያጠቃል። በተለይም ሕፃናትን፣ ለወሊድ የደረሱ ሴቶችን እና ነፍሰጡር ሴቶችን በስፋት ያጠቃል።

እጥረቱ ሰፋ ላለ የጤና እክል ይዳርጋል። ነፍሰ ጡር ሴቶች በቂ የብረት መጠን ከሌላቸው ለምሳሌ በፅንስ ላይ የአንጎል ዕድገት ተፅዕኖ እና ከኪሎ በታች መወለድ፣ ያለ ጊዜ መወለድ፣ በእርግዝና ወቅት ሞት እና ፅንስ መጨናገፍ የመሰሉ ከፍተኛ ጉዳቶችን ያስከትላል።

ጨቅላ ሕፃናት እና ታዳጊዎች በቂ ብረት አለማግኘት የረጅም ጊዜ ዕድገትን ይጎዳል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእጥረቱ ልጆች የባህሪ ችግር የሚያዳብሩ ሲሆን፤ ልጆች ደስተኛ ያልሆኑ እና እርካታ የሌላቸው እንዲሁም ከማኅበረሰቡ የመነጠል ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም እጥረቱ ከተስተካከለ ከዓመታት በኋላም የልጆች የጡንቻ እንቅስቃሴ እና የእውቀት አቅም ላይ ተፅዕኖ ይደርሳል።

የብረት እጥረት በአዋቂዎች ላይ ከዓለማችን የአካል ጉዳት መንስኤዎች አንዱ ነው። በአንዳንድ ሰዎች ላይም ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።

የተስፋፋው እጥረት

Skip podcast promotion and continue reading

የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል

የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት

ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!

End of podcast promotion

በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የሥነ ምግብ መምህር እና የንጥረ ነገሮች እጥረት ተመራማሪ የሆኑት ማይክል ዚመርማን “ትልቅ ዓለም አቀፋዊ ችግር ነው” ይላሉ።

“በጣም የተለመደ ነው። በፍጥነት የትም አይሄድም። ከብዙ የአካል ጉዳቶች ጋርም የተያያዘ ነው” በማለት ያብራራሉ።

አብዛኞቹ ተመራማሪዎች የብረት እጥረት የተለመደ እክል እንደሆነ ይስማማሉ።

ነገር ግን ከዚህ ቀጥሎ በሚመጡ ጥያቄዎች ግን ስምምነት የላቸውም።

ለአብነት ያህል የብረት እጥረት ትርጓሜ፣ ሌሎች ምልክቶች በሌሉበት እንዴት ይከሰታል፣ ከባድ ወደሆነ የጤና ችግር እንዴት ይለወጣል? በሚሉ ጥያቄዎች ለየቅል የሆኑ ሀሳቦች አሏቸው። ስለዚህ መቼ ማሟያ ወይም ደጋፊ መድኃኒቶችን መውሰድ አሊያም አለመውሰድ አለባቸው?

የማያከራክረው ጉዳይ ግን አንዳንድ ቡድኖች ከሌሎች በበለጠ ለብረት እጥረት ተጋለጡ መሆናቸው ነው።

ለምሳሌ በሴቶች ሰውነት ቀይ የደም ህዋሳትን ለመሥራት እጥረት በሚገጥምበት ወቅት የሚከሰተው የብረት እጥረት የሚከሰተው ደም ማነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የአካል ጉዳት መንስኤ ነው።

በአሜሪካ በመጀመሪያ ጊዜ የደም ለጋሾች ላይ በተደረገ ጥናት የብረት መጠን በሴቶች በ12 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን፣ በወንዶች ደግሞ ከሦስት በመቶ በታች ነው።

ይህም በመደበኛነት በወር አበባ የሚፈስ ደም ተፅዕኖን ያሳያል።

በእርግዝና ወቅት ንጥረ ነገሮች ወደ ፅንስ በመተላለፋቸው በሚያደርሰው ተፅዕኖም ሴቶች በዋናነት የዚህ ችግር ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል።

አንድ ጥናት 46 በመቶ የዩናይትድ ኪንግደም ሴቶች በእርግዝናቸው ወቅት ደም ማነስ እንደሚገጥማቸው ይፋ አድርጓል። ሆኖም ሁሉም ደም ማነስ ከብረት እጥረት የመጣ አይደለም።

አትሌቶች፣ አትክልት ተመጋቢዎች እና ተደጋጋሚ ደም የሚለግሱ ሴቶች እና ወንዶች ለብረት እጥረት የመጋለጥ ስጋታቸው ይጨምራል።

አንዳንድ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎችም ለአነስተኛ የብረት መጠን የተጋለጡ ናቸው። የኩላሊት እና ሶሊያሊክ የተባለው በሽታ የብረት መጠንን ሊቀንሱ ይችላሉ።

ቦሎቄ
የምስሉ መግለጫ,የአይረን ንጥረ ነገር ከሚገኝባቸው ምግቦች መካከል አንዱ የሆነው ቦሎቄ

ወሳኝ የእድገት ጊዜ

ሕፃናት ለብረት እጥረት በጣም ተጋላጭ ከሆኑ ቡድኖች መካከል ናቸው። ምክንያቱም ማዕድኑ ለዕድገታቸው በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ የሥነ ምግብ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑት ማርክ ኮርኪንስ “በሕይወታችን በሙሉ በጣም ፈጣኑ የዕድገት ጊዜ የትኛው ነው? የልጅነት ጊዜ ነው” ይላሉ።

በአንድ ዓመት ዕድሜ ስንወለድ ከነበረን ክብደት በሦስት እጥፍ እንጨምራለን። ቁመታችን በእጥፍ ያድጋል” ሲሉ ይገልፃሉ።

ሰውነታችን ሲያድግ የበለጠ ደም ያስፈልገዋል። ቀይ የደም ህዋስ በከፊል የሚገነባው በብረት ነው። ከአስፈላጊው ብረት ውጪ አንጎልን ጨምሮ ለኅብረ ህዋስ ዕድገት ኦክስጅን ማድረስ የሚያስችሉ በቂ ቀይ የደም ህዋሳት ለማምረት አስቸጋሪ ነው።

የብረት እጥረት በተለይም በዝቅተኛ ገቢ በሚተዳደሩ አገራት በሚገኙ ሕፃናት የተለመደ ነው። ዚመርማን “በአፍሪካ ባደረኳቸው ጥናቶች ከስድስት እስከ 12 ወር ዕድሜ ያሉ 70 በመቶ ሕፃናት በብረት እጥረት የሚመጣ ደም ማነስ አላባቸው” ይላሉ።

አጠቃላይ የተመጣጠነ ንጥረ ነገር እና በሚያመርቷቸው ምግብ በብረት የመበልፀግ ዕድላቸው ሰፊ በሆኑባቸው ሀብታም አገራትም ቢሆን እጥረቱ ይታያል።

አራት በመቶ የሚሆኑ የአሜሪካ ሕፃናት ለምሳሌ በብረት እጥረት የሚመጣ ደም ማነስ ያለባቸው ሲሆን፤ 15 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የብረት እጥረት አለባቸው።

አንድ ሰው የብረት እጥረት አለበት ማለት የደም ማነስ አለባት ማለት ላይሆን ይችላል። “የብረት እጥረት ከደም ማነስ በፊት የሚመጣ ነው” ይላሉ ሳንት-ራየን ፐርቻ የተባሉ ባለሞያ።

የብረት እጥረት እና ደም ማነስ በአጠቃላይ የደም ምርመራ ውጤት የሚታወቅ ነው።

አከራካሪው ጉዳይ

አንዳንድ ባለሞያዎች የብረት እጥረት ሁሌም አሳሳቢ ነው በሚለው ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። በተለይም ያለምንም አካላዊ ምልክት ሲከሰት እና ህሙማን ደም ማነስ ከሌለባቸው ምን ያህል አሳሳቢ ነው በሚለው ላይ ይከራከራሉ።

የዓለም ጤና ድርጅትን ለማገዝ የብረት ማሟያ ለሴቶች የሚል መመሪያ የፃፉት ሳንት-ራየን ፐርቻ የብረት ንጥረ ነገር እጥረት ያለባቸው እና ድካም የሚሰማቸው ሴቶች የብረት ማሟያ ሲወስዱ ሁኔታቸው መሻሻሉን በጥናት ለይተዋል።

በሌላ ጎን ደግሞ የብረት እጥረት ያለባቸው እና ድካም የማይሰማቸው ሴቶች ማሟያውን ሲወስዱ የኃይል መጠናቸው ለውጥ አላሳም።

በአጠቃላይ አብዛኞቹ ተመራማሪዎች በጋራ መስማማት የሚችሉት በብረት እጥረት የሚመጣ የደም ማነስ የባሰ የጤና እክል መሆኑን ነው። ነገር ግን የብረት እጥረት በአብዛኛው ከአካል ጉዳት ጋር የተያያዘ ነው።

የብረት እጥረት በሕፃናት ዕድገት ላይ በሚያስከትለው መዘዝ ምክንያት መመሪያዎች በአብዛኛው የእጥረት ምልክቶች ሲታዩ ማሟያ ወይም አጋዦችን እንዲወስዱ አሊያም አስቀድሞ ለመከላከል ማሟያውን እንዲወስዱ ይመክራሉ።

ሰዎች አመጋገባቸውን በማመጣጠን በተለይም በብረት የበለፀጉ ምግቦችን በመመገብ በቂ ብረት ማግኘት እና እጥረትን አስቀድሞ መከላከል ይችላሉ።

እንደ ጉበት፣ ቀይ ሥጋ፣ ኩላሊት፣ ጥራጥሬ፣ ባቄላ፣ ሽምብራ እንዲሁም ፍራፍሬዎች የብረት ምንጭ ናቸው።

መድኃኒቶች