November 22, 2024

 ከታሪክ ማህደር·ዜና

ከአቻምየለህ ታምሩ! ክፍል ፩]

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በሚቆጣጠረው በሸዋ ምድር በደራ ወረዳ ከሁለት ወራት በፊት ደረጀ አማረ ተስፋ የሚባል እና የ10ኛ ክፍል ወጣት የድኃ ልጅ በግፍ አርዶ በፋኖ ስም በማላከክ በአማራ ሕዝብ ላይ የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት የሚያስንቅ ሌላ ዙር የዘር ፍጅት እንዲካሄድ በሁሉም ልሳኖቹ ዘግናኝ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ እንደ አዲስ ከፍቷል።

አረመኔው የዐቢይ አሕመድ የፍጅት አገዛዝ ደረጀ አማረ የተባለውን የድኃ ልጅ የኦሮምኛ ቅላጼ ባላቸው አራጆቹ ሲያርድ የሚያሳየውን ቪዲዮ ከሰሞኑ የለቀቀው ሌላው ሕዝብ ባያምነኝ ኦሮሞ የነገርሁትን ሁሉ ስለሚያምነኝ የምፈልገውን አላማ አሳካበታለሁ ብሎ በማሰብ በአማራ ሕዝብ ላይ የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት የሚያስንቅ ሌላ ዙር የዘር ፍጅት ለመፈጸም ነው።

ከዚህ ውጭ ሰው ሁሉ ለማሰብ ፍቃደኛ እንዳልኾነው ተከታዩ ሁሉ ያለውን ሁሉ ሳይጠራጠርና ሳይመረምር እውነት ነው ብሎ የሚወስድ፤ ሳጣራትና ሳያረጋግጥ እንደወረደ የሚቀበል ስላልሆነ፣ በምርኮ የያዛቸውን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጅ የመከላከያቸውን አባላት ወደቤተሰባቸው ሲመልስ የሚውለውን ፋኖ አንድን የደራ የድኃ ልጅ በኦሮሞነቱ ይገድለዋል ብሎ የሚያስብ ጭንቅላቱን አሸዋ ውስጥ ቀብሮ አንጎሉን ያደነዘዘ ሕዝብ የለም።

አረመኔው ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የኦሮሞ ብሔርተኞች በሙሉ ያነገቡትን ጸረ ሰው አላማቸውን ለማሳካት የራሳቸውን ሰው እየገደሉ በአማራ ላይ ማላከክና ኦሮሞን ቀስቅሰው በአማራ ሕዝብ ላይ ዘግናኝ የዘር ፍጅት የመፈጸመ የኀምሳ አመታት የዳበረ ልምድ አላቸው። ይህን በማስረጃ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል።

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ሐጫሉ ሁንዴሳን የገደሉት በኦነግ ታጣቂ ቡድን ተልዕኮ የተሰጣቸው የኦሮሞ ተወላጆች መኾናቸውን በወቅቱ “ዐቃቤ ሕግ” በነበረችው በአዳነች አበቤ አማካኝነት ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በሰበር ዜና ነግሮናል።

ሆኖም ግን ሐጫሉን ራሳቸው ገድለው ሲያበቁ ግድያውን በአማራ ስም በማላከክ ኦሮምያ በሚባለው የአማራ መታረጃ ቄራ ውስጥ በሚኖረው አማራ ላይ የሩዋንዳውን የዘር ፍጅት የሚያስንቅ ፍጅት ፈጸሙበት፤ ንብረቱን አቀደሙበት፤ ከዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር እስከ ዘጠና አመት አዛውንት በጅምላ አማራ የተባለን ሁሉ በጭካኔ ጨፈጨፉት። ጅፍቱን የፈጸሙት ላለፉት አራት አስርታት ሲተረክላቸውን የኖረውን ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ለማጣራት ፍቃደኛ ያልሆኑ በአማራ ጥላቻ የሰከሩ ገዳዮች አልያም የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።

ኦነጋውያን የትግል አባት አድርገው የሚቆጥሩትን ባሮ ቱምሳን የገደለው አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ ወይም በጫካ ስሙ ጃራ አባገዳ በመባል የሚታወቀው የእስላማዊ ኦሮሚያ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ የነበረው የኦሮሞ ሸማቂ ነው። «ኦሮሞ ከፖለቲካ ሥልጣን ተገልሏል» ብሎ ኢስላማዊ ኦሮሚያን ለመፍጠር ጫካ የገባው ጃራ አባገዳ ወይም አብዱል ከሪም ኢብራሂም አሚድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛና በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የአውራጃ ገዢ የነበሩት የፊታውራሪ ኢብራሂም ሀሚድ ልጅ ነው።

ባሮ ቱምሳን ጃራ አባገዳ እንደገደለው ታሪኩን የነገረን የኦሮሞ ብሔርተኛው መረራ ጉዲና ነው። መረራ ጉዲና ይህን ታሪክ የነገረን በጦብያ መጽሔት በጥር 1988 ዓ.ም. «በመስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር በሌሎች ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ ወርዋሪ አይኾንም» በሚል ርእስ ባሳተመው ባለሁለት ክፍል ጽሑፉ ነው።

ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን የኦሮሞ ብሔርተኛት አባት የሚለው ዳኛ አሰፋ ዱላ ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ የተገደለው ከኦሮሞው ጃራ መስፍን ጋር በጥይት ተጠዛጥዘው ሲኾን ርስ በርሳቸው ተገዳደሉበት የጠባቸው ምክንያትም በመካከላቸው የተፈጠረው ቁርሾ ነው።