
24 መጋቢት 2025
ኡናላስካ ደሴት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ወታደራዊ መቀመጫ ነበር። ፓስፊክ ውቅያኖስና ቤሪንግ ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ይገኛል።
ከሰሜን አሜሪካ ወደ ሰርቢያ ሲጓዙ ነው ይህንን የአሜሪካ ደሴት የሚመለከቱት። ወደ ምሥራቅ እስያ ቅርብ ስለሆነ ከአላስካ ሩቅ ደሴቶች አንዱ ነው።
በምድር ላይ ከባድ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል። 1,100 ማይል የሚሰፋው የአሉይታን ደሴት አካልም ነው።
በቦታው አንዳችም ዛፍ ማግኘት ቀላል አይደለም። ርዕደ መሬት በተደጋጋሚ የሚነሳበት ሥፍራ ነው።
ከደሴቱ ግማሹ 70 እሳተ ገሞራዎች ይዟል። ማኩሺን የተባለው እሳተ ገሞራ ከ250 ዓመት በፊት ነበር ከመሬት ፈንቅሎ የወጣው።
ደሴቱ አውሎ ንፋስና ከፍተኛ ዝናብ ይበዛዋል። የአሜሪካና ካናዳን የአየር ሁኔታ የሚወስን አካባቢም ነው።
በደሴቱ ወደ 4,200 ሰዎች ይኖራሉ።
አብዛኞቹ ዓሣ አስጋሪ ናቸው። የደሴቱ ቀደምት ነዋሪዎች ኡኑግአክ ይባላሉ።
ላለፉት 9,000 ዓመታት በቦታው እንደኖሩ ይናገራሉ። በሕመምና በቅኝ ግዛት ምክንያት የነዋሪዎች ቁጥር የቀነሰበት ዘመን ነበር።
ወደ ደሴቱ ሩሲያውንም በስደት ተጉዘዋል።
- በርካታ አፈታሪኮች፣ ምልኪዎች እና ትንግርቶች ያሏት ሙሉ ጨረቃ12 መጋቢት 2025
- በሴቶች እና በሕጻናት ጤና ላይ ዓለም አቀፋዊ ፈተና የሆነው የአይረን ንጥረ ነገር እጥረት18 መጋቢት 2025
- በልምምድ የሚዳብረው በርካታ ፈዋሽ ጠቀሜታ ያለው የአተነፋፈስ ጥበብ15 የካቲት 2025
በታሪክ የታወቁ የመጀመሪያ የደሴቱ አውሮፓዊ ጎብኚዎች ዴንማርካዊው ቪቱዝ በሪንግ እና ሩሲያዊው አሌክሲ ቺኮቭ ናቸው።
እአአ በ1741 ደሴቱን ከጎበኙ በኋላ ሩስያውያን ነጋዴዎች ወደ ደሴቱ ያቀኑ ጀመር።
የባሕር ላይ እንስሳቱን (ሲ ኦተር እና ፈር ሲል) ለማግኘት የተጀመረው ጉዞ እአአ በ1759 ሩሲያውያን በአካባቢው ግዛት እንዲፈጥሩ ምክንያት ሆነ።
እስከ 1700 መጨረሻ ድረስ ደሴቷ በሩሲያ ሥር ቆይታለች።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነጋዴዎችን ተከትላ በደሴቱ ቤተክርስቲያን አቋቁማለች። አሁንም ድረስ በሥፍራው የሩሲያዊ ስም ያላቸው ሰዎች ማግኘት አይገርምም።

አሜሪካ አላስካን ከሩሲያ በ1867 ስትገዛ ኡናላስካ ደሴትንም ወሰደች። የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አሁንም በደሴቱ ይገኛል።
በሰሜን አሜሪካ ዕድሜ ጠገቡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው።
ቄስ ኢቮን በርስኪን ብቸኛው የኦርቶዶክስ ቄስ ሆነው ያገለግሉ ነበር።
“የዚህ ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የኔ መሆኑን ሳስብ እገረማለሁ። ታላቅ ክብርና ኃላፊነት ነው” ይላሉ።
የቤተ ክርስቲያኑን ሕንጻና ሥዕላት ለማሳደስ ገንዘብ ያሰባስባሉ።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ቀድሞ አሜሪካ የንግድና ወታደራዊ ይዞታ በሥፍራው ነበራት።
ወደ ምሥራቅ እስያ ቅርብ ቦታ ስለሆነ ለጃፓን የፐርል ሀርበር የቦምብ ጥቃት አጋልጧል።
በ1942 ሁለት የጃፓን የጦር አውሮፕላን በደሴቱ ባደረሱት ጥቃት 50 ሰዎች ተገድለዋል።
ከቀናት በኋላ የጃፓን ጦር ኪሳ እና አቱ የተባሉ በቅርብ ርቀት ያሉ ደሴቶችን ወሯል።
እንግሊዝ በ1812 ካደረሰችው ጥቃት በኋላ በአሜሪካ ምድር የተፈጸመ የመጀመሪያው ወረራ ነበር።
የአሜሪካ ባሕር ኃይል የሚጠቀምበት የመንገደኞች አውሮፕላን ላይ ጃፓን ጥቃት ፈጽማለች።
ከዚያም 145,000 የአሜሪካና የካናዳ ጦር ደሴቱን ለማስመለስ ተሰማርቷል።

ፎርት ሻዋትካ የተባለ የጦር መቀመጫ በአካባቢው ይገኛል። ርዕደ መሬትና አውሎ ነፋስ እንዲቋቋም ተደርጎ ነው የተገነባው።
በቦታው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበት ውጊያ ተካሂዷል።
በ1943 ነሐሴ ወር ላይ የጃፓን ጦር ከሥፍራው እንዲወጣ ማድረግ ተችሏል። የአሜሪካ ጦር የአካባቢው ነዋሪዎች ለደኅንነታቸው ሲባል ደሴቱን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል።
በአንድ ቀን ደሴቱን ለቀው እንዲወጡ የተነገራቸው ነዋሪዎች ከአንድ ሻንጣ በላይ መያዝ አልተፈቀደላቸውም። ወዴት እንደሚሄዱም አያውቁም ነበር።

881 ነዋሪዎች ከዘጠኝ ደሴቶች ከወጡ በኋላ ለሦስት ዓመታት በደቡብ ምሥራቅ አላስካ ኖረዋል።
ከዚያ ቀደም ከደሴታቸው ወጥተው ኖረው አያውቁም ነበር።
10 በመቶ የደሴቱ ነዋሪዎች የተደላደለ ኑሮና የጤና እንክብካቤ በማጣት ሞተዋል።
በ1945 ወደ ደሴታቸው የተመለሱ ነዋሪዎች መንደራቸው ተዘርፎና ተቃጥሎ ጠበቃቸው።
በጦርነቱ ወቅት እንግልት ከደረሰባቸው ጃፓናውያን አሜሪካውያን ጋር በመሆን የደሴቱ ነዋሪዎች መብታቸውን በመነፈጋቸው ክስ መሥርተዋል።
ኮንግረስና ፕሬዝዳንቱ ይቅርታ እንዲጠይቋቸውና የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣቸው በ1988 ፍርድ ቤት ወስኗል።
ለዚህ ጨለማ ወቅት መታሰቢያ ኃውልትም አቁመዋል።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በደሴቱ የአሜሪካ የንግድ እንቅስቃሴ ጨምሯል። በየዓመቱ ከ14 አገራት የተውጣጡ መርከቦች ዓሣ ለማጥመድ ወደ ደሴቱ ያቀናሉ።
ከአሜሪካ የዓሣ አቅርቦት 10% የሚሸፈነው በዚህ ደሴት ነው።
የዓሣ ዘይት ምርትን ጨምሮ ፈጣን ምግብ በማምረት የሚታወቁ የአሜሪካ ሬስቶራንቶች የዓሣ አቅርቦት ከደሴቱ የተሳሰረ ነው።
ዩኒሲ የተባለ የዓሣ አቅራቢ ፋብሪካ አስተዳዳሪ የሆኑት ቶም ኢንሎው እንደሚሉት፣ በአካባቢው ምንም የሚባክን ዓሣ የለም።
“የዓሣ ዘይት በመጠቀም ታዳሽ ኃይል እናመርታለን። ይህም ለአካባቢያችን ጠቃሚ ነው” ይላሉ።
በመላው አሜሪካ ካሉ የዓሣ ዝርያዎች ባጠቃላይ በዚህ ደሴት ያለው የዓሣ ዝርያ የተለየ ነው። በመጠንም ከፍተኛ ናቸው።
በአካባቢው ልዩ አእዋፋትም ይኖራሉ።
የብዙ ጎብኚዎችን ቀልብ የሚስበውም ለዚህ ነው።