ከካፌ ኬክ የምትገዛ ሴት እና ሻጭ ወንድ

ከ 3 ሰአት በፊት

መንገድ ላይ የማያውቁትን ሰው ሰላም ማለት እንደሚያስደስት ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ቱርክ ውስጥ በቅርቡ የተሠራ ጥናት የሰው ለሰው ግንኙነት ጤናማ እንደሚያደርግ ይጠቁማል።

በሳባንቺ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሰብ ሳይንስ ክፍል የጥናቱ መሪ ኤሪሳ አስጊል “ምንም ዓይነት ትውውቅ ከሌለን ሰዎች ጋር የተወሰነ ግንኙነት ስንፈጥር ደስተኛ ሕይወት እንደሚኖረን ጥናቱ ያሳያል” ትላለች።

የታክሲ ሹፌርን ማመስገን ወይም ደጋግመው የሚያዩትን ሰው ሰላም ማለት ጥሩ ስሜት ይሰጣል።

ሆኖም ግን በመላው ዓለም የማያውቁትን ሰው ማነጋገር ተገቢ እንዳልሆነ የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ራስን ምቾት የሚነሳ ወይም አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደመክተትም ይቆጠራል።

ለመሆኑ ጥቃቅን ወሬዎችን ከማያውቁት ሰው ጋር ማድረግ እንዴት ደስታ ይሰጣል? ከማያውቁት ሰው ጋር ወሬ መጀመር የሚቻለውን እንዴት ነው?

የጥቃቅን ወሬ ጠቀሜታ

በዩኬ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሰሰክስ የምትሠራው የሥነ ልቦና ባለሙያ ዶ/ር ጊሊያን ሳንድስቶርም እንደምትለው፣ ከማያውቁት ሰው ጋር ማውራት ጥሩ ስሜት የሚፈጥርና ከአካባቢያችን ጋር እንደተሳሰርን እንዲሰማን የሚያደርግ ነው።

በጥቃቅን ወሬ (small talk) ዙርያ በርካታ ጥናት የሠራችው ባለሙያዋ በቅርቡ በቱርክ የተደረገው ጥናት ውስጥም ተሳትፋለች።

“ከማያውቁት ሰው ጋር ማውራት ትስስር ይፈጥራል። በሌሎች ዕውቅና የማግኘት ስሜትም ያላብሳል። ይሄ ደግሞ የሰው ልጆች መሠረታዊ ፍላጎት ነው። ስሜታችን ላይ ብቻ ሳይሆን አካላዊ ደኅንነታችን ላይ ተጽዕኖ አለው” ትላለች።

የሥነ ልቦና ባለሙያዋ ዓይን አፋር እንደሆነች ብትናገርም ባለፉት ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ የማታውቃቸውን ሰዎች አነጋግራለች።

ሰዎችን የምታይበትን መንገድ እንደለወጠውና ሰዎች ላይ የተሻለ እምነት እያሳደረች እንደመጣች ትናገራለች።

“አብዛኛውን ጊዜ ደስ የሚል ስሜት ነው የሚፈጠረው። አንዳንዴ ምንም ላይመስለኝ ይችላል። ብዙ አዝናኝ ታሪኮች ሰምቻለሁ። ተምሬበታለሁም። ከማላውቃቸው ሰዎች ምክርና ጥቆማ አግኝቻለሁ። ሰዎችን የማይበት መንገድ ተለውጧል። የበለጠ ሰዎችን ማመን ጀምሬያለሁ” ትላለች።

ማኅበራዊ ትስስር ሰዎች የመገለል ስሜት እንዳይፈጠርባቸው ያደርጋል።

በጃፓን ሪክዮ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነው ኢታሩ ኢሺጉሮ እንደሚለው፣ ከሰዎች ተቀባይነት የማግኘት ስሜትም ይፈጥራል።

በባቡር የምትሄድ ሴት አጠገቧ ካለው ተጓዥ ጋር አብራ ስትሄድ

ከማያውቁት ሰው ጋር ማውራት ለምን ይከብዳል?

ዶ/ር ጊሊያን እንደምትለው፣ ጥቃቅን ወሬ ያለውን ጥቅም ብዙዎች አይረዱም። ትርጉም አልባና ጊዜ የሚያባክን አድርገው ይወስዱታል። ብዙዎች ጥቃቅን ወሬ ለመጀመርም ይፈራሉ።

“የሆነ ምቾት የሚነሳ ስሜት ይፈጠራል ብለው ሰዎች ይፈራሉ” ትላለች።

ኢታሩ እንደሚለው፣ ጥቃቅን ወሬ መፍጠር በሁሉም ባህል ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል የሚል ስጋትም አለ።

“በጃፓን አነስተኛ ከተማ ቶህኩ ከልጄ ጋር ስሄድ ሰዎች ‘የሚያምር ልጅ ነው’ ይሉኛል። እንደ ቶኪዮ ባለ ከተማ እንዲህ ያለ ነገር የመፈጠር ዕድሉ ጠባብ ነው” ይላል።

ከማያውቁት ሰው ጋር ማውራት ራስን ለአደጋ ማጋለጥ እንደሆነ ከልጅነት ጀምሮ ይነገረናል።

ዶ/ር ጊሊያን እንደምትለው፣ ከማያውቁት ሰው ጋር ማውራት ለአደጋ ሊያጋልጥ ቢችልም እርዳታ ማግኘት የሚቻልበትም መንገድ ነው።

ከማያውቁት ሰው ጋር ወሬ መጀመር የሚቻልባቸው አምስት መንገዶች

ከማያውቁት ሰው ጋር ማውራት ለመጀመር በባለሙያዎች የሚመከሩ አምስት ቀላል መንገዶችን እንመልከት፦