
ከ 7 ሰአት በፊት
ቢል ጌትስ እና ፖል አለን ማይክሮሶፍትን የመሠረቱት ከ50 ዓመታት በፊት ነበር።
በወቅቱ ቢቢቢ ቢል ጌትስን ሲያናግረው 130 ድረ ገጾች ብቻ ነበሩ። እአአ በ1993 የተጀመረው ማይክሮሶፍት 21ኛው ክፍለ ዘመንን ለውጧል።
ዛሬ ላይ አብዛኛው እንቅስቃሴያችን በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ ነው። ከየትኛውም ዘርፍ በላቀ የኮምፒውተር ዘርፍ እያደገ ነው።
ለተጠቃሚዎች ምቹና በቀላሉ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር መገልገያ ነው።
ማይክሮሶፍት ትልቅ ተቋም መሆን የጀመረው ከ1980 ወዲህ ነው። አይቢኤም እየሠራ የነበረውን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከገዛ በኋላ ብዙ ነገር ለውጧል።
ማይክሮሶፍት ይህንን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከገዛ በኋላ ለሌሎች ተቋማት በሽያጭ አቅርቧል። ከዛን ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስም ገቢ እያገኘበት ነው።
ቢል ጌትስ በማይክሮሶፍት ውስጥ ያለውን ሥራ ሲቀጥል አጋሩ ፖል አለን በ1983 የደም ካንሰር ስለያዘው ሥራውን ለቋል።
2018 ላይ በ65 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት እስከሚለይ ድረስ ከማይክሮሶፍት በገዛው ድርሻ አማካይነት የዓለም ሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ተካትቶ ቆይቷል።
የሚወደውን የቅርጫት ኳስ ቡድን ከመግዛት አንስቶ በተለያዩ የንግድ ዘርፎችን ተሰማርቶ ሲሠራ ነበር። ጊታር በመጫወትም ታዋቂ ነበር።
ፖል አለን ከማይክሮሶፍት ከወጣ በኋላ እንደ ዊንዶውስ፣ ኤክሴልና ወርድ ያሉትን መተግበሪያዎች ማይክሮሶፍት አስተዋውቋል።
ኮምፒውተርን ወደ መረጃ መለዋወጫ መሣሪያ መለወጥ ቀጣዩ የማይክሮሶት ሕልም ነበር።
ቢል ጌትስ በ1993 ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርግ፣ ቤት ለቤት የመረጃ መረብ መዘርጋት ቀላል እንደማይሆን ገልጿል።
“ከ15 ወይም 20 ዓመታት በኋላ በየቤቱ ኮምፒውተር ይገባ ይሆናል። አሁን ያለውን ዓይነት ኮምፒውተር ሳይሆን የወደፊቱ ኮምፒውተር የተለየ ይሆናል” ሲል ነበር ያኔ የተናገረው።
የማይክሮሶፍት ባለሙያ ናታን ማህርቮልድ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ቁጥር ውስንና ይዘታቸውም የተገደበ እንደሆነ ይሰጡ የነበሩ አስተያየቶችን በመንቀፍ እስከ 1,000 የቴሌቭዥን ጣቢያዎች የሚከፈቱበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ተንብዮ ነበር።
“አስፈሪ ይመስላል። ግን ድንቅ ነገር ነው። የምትወዱት መጽሐፍ ቤት አምስት መጽሐፍ ብቻ እንዲኖረው እንደማትፈልጉ አስቡ” ብሎ ነበር።
አሁን ላይ የተለያዩ መሰናዶዎች የያዙ ድረ ገጾች መብዛታቸውን ያኔ ነበር የገመተው።
“የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሰዎች ማየት የሚፈልጉትን በርዕሰ ጉዳይ ዝርዝር መምረጥ ይችላሉ” ሲል ነበር የማይክሮሶፍት ባለሙያ የተናገረው።
- የስማርት ስልኮች ተፈላጊነት ሊቀንስ ይችላል?18 የካቲት 2025
- ለኢንተርኔት ጅማሬ ምክንያት የሆነው ከ50 ዓመታት በፊት ያጋጠመው ግንኙነት መቋረጥ14 ታህሳስ 2024
- የኢንተርኔት አገልግሎት ቢቆም ዓለም ምን ልትመስል ትችላለች?26 ነሐሴ 2024
ዓለም በሁላችንም መዳፍ ሥር የሚሆንበት የወደፊት ዓለም ባለሙያዎቹ ቀድመው ተንብየዋል።
በ1993 ዲጂታል ሚዲያ የተባለው መጽሔት አርታዒ ዴኒስ ካሩሶ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ ነበር።
“በቴሌቭዥን ሁሉንም መረጃ ማግኘትና መቆጣጠር ወይም የምንፈልገውን ነገር ማዘዝ ማለት የኛን የግል መረጃ በኔትወርክ ውስጥ ማሳለፍ ማለት ነው” ስትል ነበር በወቅቱ የተናገረችው።
“በኔትወርኩ መነሻ ላይ ያለው ሰው ምን እያየን እንደሆነ ያውቃል። የክሬዲት ካርድ ቁጥራችንን ይወስዳል። ስለኛ እንዲታወቅ የማንፈልገውን መረጃ ባጠቃላይ ያውቃል” ስትልም ስጋቷን ገልጻለች።
ከዓመታት በኋላም የግል መረጃ አጠባበቅ ጉዳይ መነጋገሪያ ነው። ዛሬም ብዙዎች ስለ መረጃ ደኅንነት ጥያቄና ስጋት ያነሳሉ።

“መረጃ እንደ ሸቀጥ ሲሆን ሰዎች ስለ አንድ ነገር የሚያስቡበት መንገድም ይለወጣል። እንዴት እንደሚያስቡ መቅረጽ የሚቻልበትንም መንገድ ነው” ስትል አርታዒዋ አስጠንቅቃ ነበር።
መረጃ የማይጠበቅ ከሆነና እንደ ሸቀጥ ገበያ ላይ ከወጣ የሚኖውን አደጋ ገልጻለች።
ከኢንተርኔት ጋር በተያያዘ መረጃን ጠብቆ ለማቆየት የሚደረግ ጥረት ግን ፈታኝ ነው።
መረጃ ሙሉ በሙሉ ተቆልፎበት የሚቀመጥ ነገር እንዳልሆነ ትናገራለች።
“መረጃ ሙሉ በሙሉ ከተዘጋ ሳይንቲስቶች በነጻነት መረጃ መለዋወጥ አይችሉም ማለት ነው። ለሁሉም አካል መረጃ ክፍት ይሁን ከተባለ ደግሞ መረጃን የገቢ ምንጫቸው የሚያደርጉ ይኖራሉ። ቴክኖሎጂ አስደናቂ ነው። ኃያልም ነው። ኃያልነቱ አወንታዊም አሉታዊም ጎን አለው” ስትልም ታስረዳለች።
ማይክሮሶፍት እየተስፋፋ ከመምጣቱ ጋር ኢሜል ተያይዞ ይነሳል።
የተቋሙ ባለሙያ ማይክ ሙሬ ኢሜል “ዲጂታል መንደር ፈጥሯል። ጊዜና ድንበር ይሻገራ” ሲል ነው የሚገልጸው።
ሰዎች በየትኛውም የዓለም ጥግ ካሉ ሰዎች ጋር መረጃ መለዋወጥ የሚችሉበት መንገድ በመፍጠር ኢሜል ዲጂታል አብዮት አስነስቷል።
በ1993 መጨረሻ የድረ ገጾች ቁጥር 623 ደርሷል። በየሦስት ወሩ የድረ ገጾች ቁጥር በእጥፍ እየጨመረም ሄዷል።
በ1994 ቁጥሩ 10,022 ደርሷል።
በ1995 ቢል ጌትስ “ኢንተርኔት ከአይቢኤም ኮምፒውተር መፈጠር ቀጥሎ ትልቁ ግኝት ነው” ብሎ ነበር።
ማይክሮሶፍት ወርድስ 95ን የለቀቀውም ከዚህ በኋላ ነበር። ከዚያ ወዲህ ያለውን ዓለም የለወጠ ፈጠራም ሆኗል።