
ከ 5 ሰአት በፊት
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በረዳቶቻቸው እና በኳታር አለ የተባለውን ግንኙነት አስመልክቶ ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አወገዙ።
ረዳቶቻቸውን አስመልክቶ ለፖሊስ ምስክርነታቸውን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ውሃ የማይቋጥር ሲሉ አጣጥለውታል።
የኔታንያሁ አማካሪያቸው እና የቀድሞ ቃለ አቀባያቸው ሰኞ ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት “የባህረ ሰላጤዋን አገር ገጽታ ለመገንባት ገንዘብ ተቀብለዋል” በሚል የተከፈተባቸው ምርመራ ጋር ተያይዞ ነው።
ሁለቱም ባለስልጣናት ምንም አይነት ጥፋት አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብለዋል።
ፖሊስ ስማቸውን ይፋ ያላደረጋቸውን ረዳቶቻቸውን እስር “እገታ” ሲሉ የጠሩት ኔታንያሁ አክለውም “ምንም አይነት ኬዝ የለም” ብለዋል።
በሐማስ እና በእስራኤል መካከል በተደረሰው የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት ቁልፍ አሸማጋይ የሆነችው ኳታር በበኩሏ በባለስልጣኗ “የስም ማጥፋት ዘመቻ” ስትል አጣጥላዋለች።
ኔታንያሁ በእስራኤል እየተከተሏቸው ባሏቸው ፖሊሲዎች ምክንያት የተነሳባቸው ተቃውሞዎች እየተቀጣጠሉ ባለበት ወቅት ነው ይህ የተሰማው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእስራኤል ታጋቾች ከመለቀቃቸው በፊት በጋዛ ላይ እንደገና ጥቃት መጀመራቸው፣ የሺን ቤት ወይም የአገር ውስጥ የደህንንት ኤጀንሲን ዳይሬክተር ማባረራቸው እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ለማለፍ የሚያስችል አወዛጋቢ ማሻሻያ ማቅረባቸው ጋር ተያይዞ ተቃዉሞ እየገጠማቸው ይገኛል።
- የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪከ 9 ሰአት በፊት
- ከአሜሪካ ተባረው በፓናማ ሆቴል እንዲቀመጡ የተደረጉት ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎች ስደተኞች የገቡበት አጣብቂኝከ 9 ሰአት በፊት
- እስራኤል ባለፉት ሁለት ሳምንታት በፈጸመችው ጥቃት 322 ህጻናት መገደላቸውን ተመድ አስታወቀከ 8 ሰአት በፊት
በያዝነው ሳምንት ሰኞ የእስራኤል ፖሊስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እና በኳታር መካከል ያለውን ግንኙት ለማጣራት እየተካሄደ ባለው ምርመራ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸውን አስታውቋል።
ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች እንዳይወጡ ያስተላለፈውን የእግድ ትዕዛዝ ተከትሎ ፖሊስ ተጨማሪ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥቧል።
የእስራኤል ሚዲያዎች በበኩላቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ አማካሪ ጆናታን ኡሪች እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ የነበሩት ኤሊ ፍልድስቴይን መሆናቸውን ዘግበዋል። ባለስልጣናቱ ከውጭ ወኪል ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በገንዘብ ዝውውር፣ ሙስና፣ ማጭበርበር እና እምነትን በማጉደል ተጠርጥረዋል ተብሏል።
ረዳቶቻቸውን አስመልክቶ በፖሊስ ተጠይቀው ምስክርነታቸውን የሰጡት ኔታንያሁ እስሩን እንዲሁም ምርመራውን በማውገዝ በቪዲዮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
“ፖለቲካዊ ዝንባሌ ያለው ምርመራ እንደሆነ ተረድቻለሁ ነገር ግን ምን ያህል ፖለቲካዊ ነው የሚለው አልገባኝም ነበር። ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “ጆናታን ኡሪች እና ኤሊ ፍልድስቴይንን አግተው ህይወታቸውን ጭንቀት ውስጥ ከተውታል” ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊኩድ ፓርቲ የጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የሺን ቤት ኃላፊን “ኬዙን ሆን ብለው በማቀነባበር” ወንጅሏል።
በተጨማሪም “ጆናታን ኡሪችን በማሸበር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሐሰት ምስክርነት እንዲሰጥ የሚደረግ ማስፈራሪያ ነው” ብሏል።
ማክሰኞ ዕለት አንድ የፍርድ ቤት ዳኛ ጥልቅ ምርመራ የሚያስፈልገው “ምክንያታዊ ጥርጣሬዎች” አሉ በሚል የሁለቱን ባለስልጣናት እስር ለሶስት ቀናት አራዝመዋል። ፖሊስ የዘጠኝ ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቆ ነበር።
ዳኛው ሜናሄም ሚዝራሂ ሁለቱ ግለሰቦች የኳታርን ገጽታ ለመገንባት እና ስለ ግብጽ እንዲሁም በጋዛ የተኩስ አቁም ላይ ባላት ሚና አፍራሽ መልዕክቶችን በማሰራጨት መርማሪዎች እንደጠረጠሯቸው ገልጸዋል።
ለዚሁ አላማም ለኳታር የሚሰራ የአሜሪካ ሎቢ (ወትዋች) ድርጅት እና በባለስልጣናቱ መካከል የገንዘብ ክፍያ የተፈጸመበት “የቢዝነስ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አለ ብለዋል።