Mesfin Mamo Tessema

* በገና እና ታሪካዊ አመጣጡ፤

የበገና አገልግሎት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፦

እንደሌሎች የሃገራችን ጥልቅ ብሔራዊ የታሪክ ሃብቶችና በታሪክም ከእስራኤል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛ ጥንታዊ የዜማ መሣሪያ ጥንታዊ ይዘቱን የጠበቀ የሀገር ሀብት እንደ መሆኑ መጠን ሁለት ዓይነት ትርጉም አለው፡፡

እነርሱም፡-

ሰዋስዋዊ ትርጉምና

ሥነ ቃላዊ ትርጉም…………..ይባላሉ፡

የበገና ሰዋስዋዊ ትርጉም

“በገና” የሚለው ስምና “በገነ” የሚለው ግሥ በተለያዩ መዝገበ ቃላትና የቋንቋ ሊቃውንት ተተርጉሞ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ፡- አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ”መጽሐፈ ሰዋስው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ” በሚል መጽሐፋቸው በሁለት መልኩ ማለት “ሲጠቅብና ሲላላ”ብለው በማመሳጠር እንዲህ ብለው ተርጉመውታል፡፡

በገና ፡- በዕብራይስጥ ናጌን ይባላል ካሉበኋላ ሲተረጉሙት ፡- ነዘረ፣ መታ፣ ደረደረ፣ማለት ነው፡፡ ሲጠብቅ ግን ፡- ነደደ፣ ተቆጣ… ያሰኛል ብሏል፡፡

በገና፡ – በቁሙ መዝሙር ማለት ነው ብለውም ፈትተውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልደክፍሌ፡ መጽሐፈ ስዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)

አባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የትግርኛመዝገበ ቃላት በተባለ መጽሐፋቸው፡- በገናንበቁሙ በገና ብለው ተርጉመውታል፡፡ (አባዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር፣ ትግርኛ አማርኛመዝገበ ቃላት፣ 1948፣አሥመራ)

ከሳቴ ብርሃን ተሰማ “የአማርኛ መዝገበቃላት” በተሰኘ መጽሐፋቸው እንዲህ ዓይነትትርጉም ሰጥተውታል፡፡

በገና፡- በአሥር አዉታር ጅማት በገናን ሠራ፣ቃኘ፣ ደረደረ፣ ድምጽን እያጣራ፣ እያጣቀሰ፣እየነዘረ… በገናን በገነ… ካሉ በኋላ በገነኛ፡-የሚለው ደግሞ በገናንየሚመታ፣ በገናንየሚያውቅ ደርዳሪ… ማለት ነው ብለውተርጉመውታል፡፡ (ከሳቴ ብርሃን ተሰማ፣የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ 1951 ዓ.ም፣አርቲስቲክማተሚያ ቤት፣ አዲስ አበባ)

የበገና ሥነ ቃላዊ ትርጉም፡-

በገነ፡- አደረቀ፣ አቃጠለ፣ አነደደ… ማለት ነው፡፡በገናም ከዚህ የሚወጣ ስም ነው፡፡ የዚህትርጉምማግኘት ዋና ምክንያትም ሁሉም ነገር (የበገናሁለገብ ሰውነት) በደረቅ ነገሮች ማለትምበደረቅእንጨትና በደረቅ ቆዳ እንዲሁም በደረቅ ጅማትየሚሠራ ወይም የሚዘጋጅ ስለሆነ በገና ተባለተብሎ ይተረጐማል፡፡

በገና፡- “በ” እና “ገና” በመነጣጠል የሚያስገኘውትርጉም በመጠቀም… በ … ገና…. በገና በዓልወይ በገና ወቅት የሚደረደር የምስጋና መሣርያስለሆነ በገና ተባለ ተብሎ ይተረጎማል፡፡

በገና፡- በገነ ማለት ደረደረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነምበገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር… ማለትነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በማድረግይተረጎማል፡፡

ለምሳሌ፡-

“አቤቱ አምላኬ በበገናአመሰግናለሁ” መዝ.42/43፡4

“ለእግዚኣብሔር በገናደርድሩለት” መዝ.48፡5

“እግዚኣብሔርንበመሰንቆ አመስግኑትአሥር አውታር ባለውበበገና ዘምሩለት”መዝ.32/33፡2

የዚህ አጭር ጥናታዊ ጽሑፍ ኣቅራቢ ግንከሁለቱም ወገን በሚወሰዱ የትርጉም መመሳሰልበመነሳት በምስጢር ከበገና መንፈሳዊናማኅበራዊ አገልግሎትጋር የተሻለ ቀረቤታ ያለውንትርጉም ቢሆን ይመርጣል፡፡

በመሆኑም፡- በገነ፡- ደረደረ፣ መታ፣ አነዘረ…. ወዘተማለት ነው በሚለው መልካም ትርጉምይስማማል፡፡ ምክንያቱም ከነባራዊ የበገናማኅበራዊም ሆነ መንፈሳዊ እሴት ማለትምከድርጊቱ ወይም ከአቀራረቡ (ከአገልግሎቱ) ጋርአብሮ ይሄዳልና ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት፡-

በገና፡ -ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር…ወዘተ ማለት ነው፡፡ በገነኛው ቅዱስ ዳዊትበመዝሙሩ በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ምስጋና… በማለት ሲገልጽ እናገኘዋለንና፡፡

የበገና ታሪካዊ አጀማመር፡-

በገና፡- በትክክል መቼና እንዴትተጀመረ የሚለውጥያቄ መልሱ ከባድ ቢሆንም ሁላችንምእንደምናውቀው፣ ዓለምም ቢሆን በስፋት በግልጽበአደባባይ እያወደሰው እንዳለ የሁሉም ጥበባትማለትም ሥጋዊ ጥበብንም ጨምሮ መገኛቸውወይም ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡በመሆኑም በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜተገል ጾ የምናገኘው የምስጋና ወይም የዜማመሣሪያ በገና ብቻ ነው፡፡

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እውነታ የመረመርነው እንደሆነ፡-

በገና ለመጀመሪያ ጊዜ የደረደሩት የላሜህ ልጅየዩባል /ኢዮቤል/ ልጆች ነበሩ (ዘፍ.4፡19-24)፡፡ይኸውም ዓይነ ስውር (ማየት የተሳነው) የነበረላሜህ አያታቸው በበረሃ እየሄደ እያለ ቃኤልተቅበዝባዥ ነበርና ለብቻው በዱር ተሰውሮሲንኮሻኮሽ ሰምቶ መንገድ ይመራው ለነበረውረድእ “እጄ ይሞቅብኛል ቅጠሎች ሲንኮሻኮሹእሰማለሁ አራዊት መጥቶብናል መሰለኝ ስለዚህድንጋይ አቀብለኝ” ኣለውና ድንጋዩን ተቀብሎቢወረውር የቃየን ግንባሩን መትቶ ገደለው፡፡ቀርበው ሲመለከቱት የራሱ አባት ቃየን ሆኖሲያገኘው እጅግ መሪርየሆነ ለቅሶ አለቀሰ፡፡ ወደቤቱ ተመልሶም ዓዳና ሴላ ለሚባሉት ሚስቶቹ″ስምዓኒ ዓዳ ወሴላ አንስትያየ አነ ቀተልክዎለቃየን አቡየ፡- ዓዳና ሴላ ሚስቶቼ ሆይ ስሙኝ፤እኔ ዛሬ አባቴ ቃየንን ገድየዋለሁና….” በማለትነገራቸው፡፡ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ታሪካዊተዋረዱን ጠብቀው የታሪክ እውነታውንለልጆቻቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም የላሜህ የልጅልጆች (የዩባል ልጆች) በቃየን ሞት ብቻሳይሆንበወላጆቻቸው የአሟሟት ሁኔታ እጅግ አዘኑ፡፡ይህም አቤል በቅንዓት ምክንያት በገዛ ወንድሙበቃኤል መገደሉ፤ ቃየንም “ተባርዮን የማያስቀርአምላክ ነውና” በገደለው ዓይነትየአገዳደል ዘይቤበድንጋይ በልጁ በላሜህ መሞቱ… እያወጡእያወረዱ እጅግ ከማዘናቸው የተነሳ በገናለመጀመርያ ጊዜ ከደረቁ ቁሳቁሶች አበጅተውበመሥራት በበገና እያንጎራጎሩ ሐዘናቸውንገልጸዋል፡፡

በዚህም በገና ከፍጥረተ ዓለምብዙም ባልራቀሁኔታ (ከአዳም አምስተኛ ልጆች በሆኑ አበው) የተገኘ የመጀመርያ የሐዘን፣ የእንጉርጉሮ፣ የንስሐ፣ የልመናና የምስጋና መሣሪያ ነው እንላለን፡፡ ተዋረዱም፤

አዳም፡- ቃኤልን ይወልዳል ቃኤል፡- ላሜህንይወልዳል ላሜህ፡- ዮባልን ይወልዳል ዮባል፡-በገና የሚደረድሩትን ይወልዳል (ስማቸውበመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አልተገለጸም)፡፡በመሆኑም የአራተኛ ትውልድ ልጆች ማለትምከአዳም አምስተኛ ትውልድ በሆኑት በእነዚህአበው ምክንያት በገናን ተዘጋጅቶ መደርደርተጀመረ፡፡

ቃለ በገና፡- ቃለ ማኅዘኒ

ድምፀ ማኅዘኒ … ነው፡፡ ምክንያቱም በተለይየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንሊቃውንት አራቅቀው እንደሚተረጉሙት ይህምድራዊ ማኅዘኒ ዜማ የመጣው በዮባል ልጆችኃዘንና እንጉርጉሮ ምክንያት እንደሆነ ይኸው ከላይየተጠቀሰው ታሪክ ጠቅሰው ያትታሉ፣ያመሰጥራሉ፡፡ ይኸውም ከላይ እንደተገለጸው፡-ቃየል ወንድሙ አቤልን መግደሉ፤ ቃየል ደግሞበልጁ በላሜህ መገደሉን፤ እያስታወሱ የዩባልልጆች የደረቀ እንጨት ጠርበውና አለዝበው፣ ቆዳወጥረው፣ ፍቀው፣ አድርቀውና ዳምጠው፣ ጅማትአክርረውና አበግነው… በቃለ ማኅዘኒ፣ በድምፀማኅዘኒ… ያንጐራጉሩ ነበር በማለትሊቃውንቶቻችን ያትታሉ፡፡

በዚህ ታሪካዊ እውነታምክንያት ነው “በገና” ቃለ ማኅዘኒ፣ ድምጸ ማኅዘኒሆኖ የሐዘን ማለትም የንስሐ፣ የልመናና የምስጋናማቅረቢያ የዜማ መሣሪያ በመሆን አገልግሎትበመስጠት ላይ የሚገኘው፡፡ የበገና የአጀማመሩታሪክ በዩባል ልጆች ቢሆንም ዘመናት አልፎከትውልድ ትውልድ ሲተካ ይዘቱም ሆነ ዓይነቱእየተሸሻለ መጥቶ የበገና አጠቃላይ ማኅበራዊሚናውም ሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ይበልጥጎልቶ የታወቀው ግን በመዝሙረኛው (በበገነኛው)በቅዱስ ዳዊት ምክንያት ነው፡፡

የበገና አገልግሎት፤

በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊትሩፋትማለትም ለምስጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡በመሆኑም ተመርጦ ለቤተክርስቲያን አገልግሎትይውላል፡፡ ለምሳሌ፡-

“አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ”መዝ.42/43/4

“አሥር አውታርም ባለው በበገናዘምሩለት” መዝ.32/33/2

“ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት”መዝ.4.8/5/… ወዘተ ከተመዘገቡትመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃዎች ጥቂቶቹናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱለማኅበራዊ እሴት፣ ለሃገር ክብር፣ ለሉዓላዊነት…በገና ይደረደራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማስረጃችን በአፄቴዎድሮስ ጊዜ የተደረደረውና እስከ አሁን ድረስየበገና መማርያ የሆነው የበገና አገልግሎት ነው፡፡ከዚህ ውጭ በገና ለዓለማዊ ፍላጐትማስፈጸሚያ ማለትም፡- ለዳንስና ለዳንኪራለዘፈንና ለጭፈራ ለዝናና ለጉራ ለቀልድና ለፉከራ… ወዘተ ፈጽሞ አገልግሎት አይሰጥም፡፡

የበገና ጥቅም፡-

ከላይ እንደተገለጸው በገና በዋናነት ለመለኮታዊየእግዚአብሔር ፈቃድ ማስፈጸሚያማለትምለምስጋናና ለልመና የሚያገለግል ሲሆንበተጨማሪም ለማኅበራዊ እሴት መግለጫየሚውል መንፈሳዊና ጥንታዊ የዜማ መሣሪያነው፡፡

ስለ በገና በመጽሐፍቅዱስ የተጻፉ በአብዛኞቹ የሚገልጹት “በገናለምስጋናና ለልመና ሲቀርብ” ነው።

ትንቢት ለመናገር

ቅዱስ ዳዊት የተናገራቸው ቃለ ትንቢቶች በሙሉ መመልከት ወይም ማንበብ በቂ ነው፡፡

“ወደዚያም ወደ ከተማይቱ በደረስህ ጊዜ፥ በገናና ከበሮ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኮረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያት ጉባኤ ያገኙሃል” 1ኛ መ. መሳ. 10፡5

ከመናፍስት ሥቃይ ለመዳን

“እንዲህም ሆነ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፡፡ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር” (1ኛሳሙ.16፡23) እንዲል፡፡

የሀገር ሉዓላዊነት ለመግለጽ … ወዘተ ይጠቅማል፡፡

“ፈረሱ አባ ታጠቅ ስሙ ቴዎድሮስ….. እኔ መዩ ቱርክን ባይ የምሸሽ ነኝ ወይ….” እንደ ምሳሌ ልንወስደው እንችላለን፡፡

በገና ወደ ሀገራችን እንዴት መጣ?

የበገና ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የአመጣጥ ታሪክ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡

የሀገራችን ኢትዮጵያ የሥልጣኔዋ ውጤትና በሕገ ልቡና የማመንዋ ውጤት ነው፡፡ /የተጀመረ እዚሁ ሀገራችን ነው የሚል አስተምህሮ ነው፡፡/

በቀዳማዊ ምኒሊክ ጊዜ ከታቦተጽዮን ጋራ አብረው ከመጡት የዜማና የሥርዓተ አምልኮ ንዋያተ ቅድሳት፣ መጻሕፍት… ወዘተ አንድ ሆኖ የመጣ ነው የሚሉ ሲሆን ይህንኑ አመለካከትም ይበልጥ በሀገራችንጠበብት ሊቃውንት በስፋት ይተረጉማል፣ ይተረካል… ይታመናልም፡፡ [ atronsmedia.com ]